Πέμπτη 24 Ιουνίου 2021

Zombies of Nairobi! - The story of Kenya's liquid drugs and their impact on street children

 


"In the second episode of Toxicity we take you among Nairobi's street kids, turned into zombies by lethal sniffing drugs such as glue and jet fuel, which they inhale hundreds of times every day. 

These drugs mess with their brain functions and transform them into junkies incapable of controlling their mind and body. 

Report by Pablo Trincia".

Please, see the video here!

Four of the readers' comments

This guy has guts. I'm Kenyan and I'd never step foot on the places this guy went to film this.

Never felt this bad watching a documentary. This is more impactful than Vice.

They really went for a Narcos opening but I don't blame them.

They're doing drugs so that they don't feel the hunger. This is so sad and depressing.
"Children are the future of our society", just wonder how bleak the future is. 

 


Τετάρτη 23 Ιουνίου 2021

በወቅታዊው የኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ግጭት ላይ -አስመልክቶ የቀረበ ክርስቲያናዊ {የፍቅር} ጥሪ

 


OODE - ኦርቶዶክሳዊ ትምህርተ ዶግማ መድረክ

In English: A Christian Plea for Love: On the Current Conflict in Ethiopia's Tigray Region

በጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ጀመረ  በመጀመሪያዎቹ አምስት ወራቶች ላይ በሰላማዊ ዜጎች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት መፈፀማቸው ጨምሮ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሪፖርቶች የወጡ ሲሆን ሰላማዊ ዜጎች ላይ ማለትም ወንዶችና ልጆችን መግደል እንዲሁም በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ ወሲባዊ እና ጾታ ተኮር ጥቃቶችን ማድረስን ያጠቃልላል (እንደነዚህ ያሉ የወንጀል ዘገባዎች በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ በተባበሩት መንግስታት፣ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና በሌሎች ተአማኒ ምንጮች ተረጋግጠዋል፤ ስለሆነም  እዚህ ላይ ድጋሚ መጥቀስ አያስፈልግም)

እኛ ክርስቲያኖች በዓለም ላይ ሁሉንም ሕዝቦች የሚነካ ሁከት ሁሉ ያሳስበናል፣ ይህም ስንል በትግራይ ተወላጆች እና በሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈፀመ ያለውን ሁከት (በትግራይ ክልል ማይ ካድራ ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ እና በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ እና በኦሮምያ ክልሎች ጨምሮ በሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች የተከሰቱ ሁከቶች ማለታችን ነው  በትግራይ ክልል በሰላማዊ ዜጎች ላይ ስለተፈፀሙት ወንጀሎች እና በመሠረተ ልማቶች ላይ የደረሰው ውድመት ያስከተለውን ሰብአዊ ቀውስ ለመግለፅ አዳጋች ከመሆኑም ባሻገር ንጹሐን ዜጎች በረሃብ እና በመድኃኒት እጦት የመሞት ዕድልን ከፍ ያደርገዋል

አሁን ባለው ግጭት በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈፀመው እና እየተፈፀመ ያለው ወንጀል በኢትዮጵያውያን ዘንድ አቅሎ ማየቱ ወይም እንደ አይቀሬ የጦርነት ውጤት ተደርጎ መታየቱ ከልብ ያሳስባል የበለጠ ግራ የሚያጋባው ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ፖለቲከኞች እና የሚዲያ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ህወሓትን እና የትግራይን ሕዝብ አጠቃልሎ እንደ አንድ ማየታቸው ነው  የትግራይን ሕዝብ እራሱ በታሪክ ያጋጠሙትን የፍትሕ እጦትና ግፍ ችላ በማለት ሥልጣን ላይ ያሉትን እና ተራውን ሕዝብ ድሃውን ሕዝብ መለየት አልቻሉም በሕዳር ወር 2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ ዋና ከተማ ውስጥ ለአንድ ወር ያህል በቆየንባቸው ጊዜያት ከብዙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለመገንዘብ እንደቻልነው ጦርነቱ በታሪክ ኢ-ፍትሐዊ እና ወንጀለኞች ብለው ከሚያስቧቸው የህወሓት ካድሬዎችን በማገናኘት ፍትሐዊ እና ተገቢ ጦርነት እንደሆነ አድርገው የሚቀበሉት ብዙ ሰዎች እንዳሉ አይተናል ሌሎች ደግሞ እንደ ባሕርያዊ በመውሰድህወሓትን በማድቀቅ ሂደት ውስጥ ንጹሐን ዜጎች መሞታቸውየማይቀር ክፉ እጣ” እንደሆነ አድርገው ይገልጹታል  እነዚህ አመለካከቶች ከታሪካዊ ቅሬታዎች የሚመነጩና አንድ ዓይነት ፍትሕ ይፈልጉ እንደነበር ለመገመት ባያዳግትም  በቀልን በበቀል መሻት ግንምን ያህል ችግር እንደሆነና ምን እንደሚያስከትል በአግባቡ አልታየም ወይም ፍትሕ በጦርነት ከኦርቶዶክስ እምነት (አብዛኛው ሕዝብ ነኝ ከሚለው እምነት) አንጻር ምን እንደሆነ በጭራሽ አልተመረመረም።

ግጭቱ ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርገው ደግሞ አንዳንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሃይማኖት አባቶች እና ቃል አቀባዮች የሰጡት ምላሽ ነው ግጭቱ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ዘር/ጎሳ ዋነኛ መለያያ ምክንያት መሆኑ ግልጽ ሆኗል  ለዚህ እንደ ማረጋገጫነት ደግሞ አንድ አንድ ካህናት እና ዲያቆናትን ጨምሮ የቤተክርስቲያኗ አባላት - ሰላም ወዳዶችለመሆን ቃል የገቡ እና በምእመናኖቻቸው መካከል ሰላምን ለማስጠበቅ የራሳቸውን ሕይወት አሳልፈው ለመስጠት መዘጋጀት እንዳለባቸው ዘንግተው - ግጭቱን ለመባረክ እና ወታደራዊ እርምጃውን ለመደገፍ አላቅማሙምእንዲሁም ታሪካዊ እና ፖለቲካዊ ቅሬታዎች እናየአገር ፍቅር” የሚል የተዛባ ግንዘቤ እንደ ምክንያታቸው አድርገው ያቀርባሉ ይህም የሚያሳየው እንደዚሀ ያለ አቋም በሚይዙት ዘንድ ያለው የ "እምነት" ትርጉም መዛባቱን ያሳያል ስለሆነም እዘህ ላይ ሊሎች መዛባቶችለመፍታትና ለማስቀረት የኦርቶዶክስ እምነት የቆመችለት ነገርምን እንደ ሆነ  እዚህ ላይ ማስታወስያስፈልጋል

ክርስቲያኖች እንደመሆናችን መጠን የሰውን ልጅ ሕይወት አደጋ ላይ ከሚጥሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሁሉ መራቅ አለብን  የውጭ ዜጎች እንደመሆናችንም መጠን በኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ፣ ሙስናን እና የወንጀል ድርጊቶችን ለመቅረፍ የሚደረጉ ጥረቶችን መቃወም የእኛ ተልእኮ አይደለም ከምንም በላይ ደግሞ የሉዓላዊነት ጉዳይነው ሆኖም ግን እንደ ክርስቲያን ኦርቶዶክስ አማኞች ዓመፅን በመጠቀም ክፋትንለማረም የሚደረገውን ድርጊት ችላ ማለት አንችልም። እምነታችን ማነኛውን ዓመፅ አይደግፍም፤እኛ ላይ በደረሰብን ግፍም ተነሳስተን በቀልን መፈለግ እንደሌለብን ያስተምራል ለተሳሳተ ድርጊት ዕዉራን መሆን የለብንም፣ በምንችለው በሰው ልጅ ዓቅማችን ደግሞ ስሕተቱን ለማረም እና  ማሕበረሰብ ውስጥ ፍትሕን ለማስፈንመጣር ቢኖርብንም፣ ቅዱስ የሆነውን የእግዚአብሔር አምሳል በሌሎች ላይ በማየት የምንችለውን ምሕረት እንድንሰጥ እና የበቀል እርምጃ መውሰድ እንደሌለብን ታዘናል  ለምሳሌ በሮሜ 12፡ 17 ላይ እንዲህ ተብሎ ተጽል:-

ለማንም ስለክፉ  ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ።

በ1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5፡ 15 ላይ እንዲህ ይላል:-

ማንም ለሌላው በክፉ ፈንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፥ ነገር ግን ሁልጊዜ እርስ በርሳችሁ ለሁሉም መልካሙን ለማድረግ ትጉ።

እምነታችን እግዚአብሔርን ብቸኛ ፈራጅ አድርጎ ያምናል፣  ፍቅርና ሁሉን አዋቂ የሆነው እርሱ- የሰው ልጆች በማይችሉትን በዓለም ላይ ፍጹም ፍትሕን ሊያመጣ የሚችል ነው። እግዚአብሔር የሰውን ሕይወት ለመጠበቅ እና በሕብረተሰቡ ውስጥ ሕጋዊነትን ለማስፈን ሰው ሠራሽ የፍትሕ ሥርዓቶችን ሰዎች መጠቀማቸው አይቃወምም፣ ግን ማሕበራዊ ፍትሕን ለማስፈን ሲባል በልጆቹ መካከል አለአግባብ ኃይልመጠቀምን አይቀበልም የሰው ልጆች እርስ በራሳችን ካልተዋደድን እግዚአብሔርን እንወዳለን ማለት እንደማንችል መጽሐፍ ቅዱስ በግልፅ ይነግረናል፣ ይህ ማለትም ጠላቶቻችን ናቸው ብለን የምንቆጥራቸውንምእንኳን መውደድ አለብን ማለት ነው በሮሜ 13፡ 8-10 እንደተባለው

እርስ በርሳችሁ ከመዋደድ በቀር ለማንም ዕዳ አይኑርባችሁ፥ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሞታልና። አታመንዝር፥ አትግደል፥ አትስረቅ፥ በውሸት አትመስክር፥ አትመኝ የሚለው ከሌላይቱ ትእዛዝ ሁሉ ጋር በዚህ። ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ በሚለው ቃል ተጠቅልሎአል። ፍቅር ለባልንጀራው ክፉ አያደርግም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው።

ውስን እውቀት ጉድለት ያለን የሰው ልጆች እንደመሆናችን መጠን ድርጊቶቻችን ምን ውጤት ሊያስከትሉ እንደሚችሉ መገመት አንችልም፣ ለዚህም ነው ከበቀል ተግባራት መታቀብ ያለብን  አንድን እንደ ጥፋት ያሰብነውን ድርጊት ለማስቆም ዓመፅን በመጠቀም ፍትሕ ያስገኛል ብለን እናምን ይሆናል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ ጠላት (ሰይጣን) እና አገልጋዮቹ ዕድሉን በመጠቀም የበለጠ ክፋትን ለመፈፀም መንገድ ያገኛሉ በትግራይ ውስጥ እየተካሄደ ባለው ጦርነት የፌዴራል ወታደሮች  አስገድዶ መድፈርን እንደ አንድ መንገድ የሚጠቀሙ ሲሆን ይህም በተጎጂዎች / በሕይወት የተረፉ እና በቤተሰቦቻቸው ላይ ለመግለፅ የሚያዳግት አካላዊ፣ ሥነ ልቡናዊ እና ስሜታዊ ጉዳት አድርሷል የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲህ አይነቱ ፍትሕን ነው ያስብ የነበረው ወይም ይህ እንዲፈጠር ነው ተስፋ ያደረገው? በእርግጥ ይህንን ክፋት አላቀዱበትም ይሆናል፤ ይሁን እንጂ ጦርነቱ ባገኘው ድጋፍ እግዚአብሔርን በማይፈሩ እና ሌሎችን ለመጉዳት ወደኋላ በማይሉ ሰዎች የጭካኔ ድርጊቶች እንዲፈጠሩ ዕድል ፈጠሯል

እምነታችን በቀልን በበቀል መመለስ እንደሌለብን ያስተምረናል፤ ይህም በዋናነትበልባችን ውስጥ ቂም ከያዝንና በትዕቢት እኛም እንደ እግዚአብሔር ሌሎች ምን ዓይነት ፍትሕ እንደሚገባቸው እናውቃለን ብለን ካሰብን ልናሳካቸው ስለማንችላቸው ስለመንፈሳዊ እድገታችንና ስለድኅናታችን ሲባል ነው። የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ለኃጢአት የተጋለጥን የሰው ልጆች እንደመሆናችን መጠን ስለራሳችን ኢ-ፍጹምነት እና ውስንነቶች በትሕትና ግንዛቤን ማሳደግንታስተምራለች ስለሆነም እግዚአብሔር እኛን እንዲረዳን እና ኃጢአታችንን ይቅር እንዲለንና እንዲያዝንልን እንደምንፈልግ ለሌሎች ፍቅር እና ሐዘኔታ እንድናሳይ ታሰገነዝበናለች። ይህ ማለት ግን ማሕበራዊ ፍትሕን ለማምጣት የሚደረገው ጥረት አንደግፍም ማለታችን አይደለም፣ እንዲያውንም መደገፍ ይገባናል፣ ግን በኦርቶዶክሳዊ ሕሊና እና አስተሳሰብ (“ፍሮ”) ለሰው ልጆች ርህራሄ እና አሳቢነት በሞላበትና ዓመፅ ዓመፅን እንደሚወልድ በመረዳትና ዓመፅን ባራቀ መልኩ ማድረግ አለብን  ለማለት ነው

 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በግልፅና በማያሻማ መልኩ ENCOMIASTIC ESSAY ON THE HOLY MARTYR PHOCAS AND AGAINST HERETICS፡” በሚለው ጽሑፉ እንደ ሚከተለው ያስቀምጠዋል:-                                        

Διότι τέτοιος είναι ό δικός μας πόλεμος· δέν καθιστά τούς ζωντανούς νεκρούς, άλλά τούς νεκρούς τούς όδηγεΐ στή ζωή, γεμάτος άπό ήμερότητα και πολλή έπιείκεια.

የእኛ ጦርነት ሕያዋንን መግደል አይደለም፤ ይልቁንም በየዋህነትና ትዕግስትበተሞላበት ሕይወት አልባዎችን ወደ ሕያዋን መመለስ ነው

Δική μου συνήθεια είναι νά καταδιώκομαι καί όχι νά καταδιώκω, νά πολεμούμαι καί νά μή πολεμώ.

እኔ  መሰደድ እንጂ ማሳደድ መወጋት እንጂ መውጋትልማዴ አይደለም

በየመከላከል ጦርነቶች ላይ ዜጎች እራሳቸውን ቤተሰቦቻቸውን እና አገራቸውን ከወራሪዎች ለመከላከል የጦር መሣሪያ እንዲያነሱና እንዲጠብቁ በሚጠሩበት ወቅት እንኳን እምነታችን ዓመፅ መጠቀምን አያስተምርም አይደግፍምም። ለምሳሌ፣ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የኩይንሴክስት ጉባኤ (Quinisext Council of the Orthodox Church) የታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ  ሁለት ቀኖናዎችን አፅድቋል፣ አንደኛው በጦርነት ጊዜ በምንክላከልበት ጊዜ እንኳን ሳይቀር የሰዎች መግደልን የተመለከቱ የውግዘት ሕጎችን ያጠቃልላል (“ቤተክርስቲያኗ ወታደራዊ መሣሪያዎችን ትባርካለች ወይ?” የሚለውን ይመልከቱ)  በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ብዙ ጠንካራ እምነት ያላቸው ወታደሮች ወታደራዊ ችሎታቸውን ተመክተው ከመዋጋት ይልቅ ሰማዕትነትን መርጠዋል፡፡ (ለተጨማሪ ምሳሌቤተክርስቲያኗ ወታደራዊ መሣሪያዎችን ትባርካለች?” ይመልከቱ)  እነዚህ ወታደሮች የሌላውን ሕይወት  ክርስቲያን ያልሆነ የጠላት ሕይወት ጭምር ከማጥፋት ይልቅ ሕይወታቸውን መሥዋዕት ለማድረግ ስለመረጡ በቅዱስና የተከበሩ ናቸው። እነዚህ የኦርቶዶክስ አማኞች እምነታችን ያልፈጥርነውንና የማንቆጣጠረውን ሕይወት ማለትም ለሁሉም ሕይወት ቅድስና እንደቆመ በሚገባ ያውቁ ነበር  ሕይወትን እኛ ስላልፈጠርናትየመውሰድ መብት የለንም ብቸኛው ሕይወት  ሰጪ እግዚአብሔር ስለሆነ መውሰድም ያለበት እግዚአብሔር ብቻ ነው

እምነታችን በደረሰብን ኢፍትሐዊነት በቀልን መፈለግ እንደሌለብን በግልጽ ይናገራል አንድ ሰው ያለአግባብ ፍትሕን ቢያጓድልብን እግዚአብሔር በእኛ ላይ የተፈጸመውን ኢፍትሐዊነት ፍትሐዊ እና ለእኛ እና ለእነሱ መዳን በሚጠቅም ስለሌሎች በሚያስብ መንገድ እንደሚመልስልን የተረድዳ ነው። ነገር ግን በሌላው ላይ ግፍን የምንፈፅም ከሆነ፣ ይህ መጀመሪያ በራሳችን ብሎም በልጆቻችን መከራና ስቃይ መቃናትና መታረም ሊኖርበት ግድ ይላል። ይህም እኛን ለድኅነታችን አስፈላጊ ወደሆኑት ወደ ንስሐ ኣንዲመራን፣ የተማርንና ትሑታን እንሆን ዘንድ ነው።

በቀልን የምናሸንፍበት ትልቁ ማረጋገጫችን ለሰው ልጆች መዳን በመስቀል ላይ ለመሞት በፈቀደውበጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጠን እምነታችን ነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰዎች ተከዳ፣ ተበደለ እንዲሁም ተገደለ፤ ይህም ግፍ አድራጊዎችን ማስቆምና መበቀል ቢፈልግ  ወይም ቢሻ ማድረግ ቢችልም እንኳን ግን አላደረገም በምትኩ፣ የሰማይ አባቱን በደለኞችን ይቅር እንዲል በመጠየቅ በደልን ለመቀበል መርጧል እናም ፍጹም -ፍትሐዊ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ  እንኳን ራስን መሥዋዕት ማድረግ እና ይቅር ባይ መሆንን በተግባር አሳይቶናል።

ስለዚህ ጉዳይ በድጋሚ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በርትዓት ለቅዱስለጀግናው ሰማዕት ለቅዱስ ፎቃስ “ENCOMIASTIC ESSAY ON THE HOLY MARTYR PHOCAS AND AGAINST HERETICS” በሚለው ጽሑፉ እንደሚከተለው አስፍሯል:፟-

’Έτσι καί ο Χριστός ήρθε στον κόσμο όχι γιά νά σταυρώσει αύτόν, άλλά γιά νά σταυρωθεί* όχι γιά νά δώσει ράπισμα, άλλά νά δεχθεί ράπισμα.

Ο Κύριος της οικουμένης άπολογεΐται στο δούλο τού άρχιερέα καί δέχεται ράπισμα στο στόμα έκεΐνο άπό τό όποιο βγήκε ό λόγος έκεΐνος πού χαλιναγώγησε τή θάλασσα, ό λόγος έκεΐνος πού άνέστησε άπό τούς νεκρούς τον τετραήμερο Λάζαρο* μέ τό όποιο άπομάκρυνε τήν κακία, μέ τό όποιο έλευθέρωσε άπό νοσήματα καί άμαρτήματα. Αυτό είναι το άξιο θαυμασμού έκείνου πού σταυρώθηκε. Ένώ δηλαδή μπορούσε νά ρίξει κεραυνό, νά σείσει τή γη καί νά ξηράνει τό χέρι τού δούλου, τίποτε άπό αύτά δέν έκαμε, άλλά καί άπολογεΐται καί νικάει μέ τήν πραότητά του, διδάσκοντας έσένα πού είσαι άνθρωπος νά μή άγανακτεΐς ποτέ.

ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም የመጣው ዓለሙን ሊሰቅል ሳይሆን ሊሰቀል፤ በሌሎች ላይ ብትር ለማሳረፍ ሳይሆን የብትር መከራ ሊቀበል ነው

ዓለም ጌታ የሊቀ ካህናቱን አገልጋይ {በአፉ} ተማፀነ። ነገር ግን ባሕርን የገሠጸበት፣ ከሞተ አራት ቀን የሆነውን አልዓዛርን ከሙታን ያስነሣበት፣ ክፋትን ያስወገደበት፣ ከደዌና ከኃጢአት ነፃ ያወጣበት ቃሉ የፈለቀበት አፉ ከሊቀ ካህናቱ አገልጋይ ጥፊ ተቀበለ። ይህ በተሰቀለው ላይ የደረሰው ተደሞ የተገባው ነው። ይህም በመብረቅ ጥቃት መሬትን ማንቀጥቀጥና የዚያ አገልጋይ እጅ ሽባ ማድረግ የሚችል ነው። እርሱ ግን ከእነዚህ አንዱን ስንኳ አላደረገም። ይልቁንስ በዚህ ፈንታ ለመነ በየዋህነቱም አሸነፈ፤ በዚህም ሰው የሆንከው/ሽው አንተን/ቺን ፈጽሞ እንዳትቆጣ/ ያስተምርሃል/ሻል።

ራሱን ለመሥዋዕትነት በማቅረብና ለደረሰበት ግፍና በደል ለበዳዮቹ ይቅርታን በመለመን  ውሳኔው ውስጥ ክርስቶስ ወሰን የሌለው የእግዚአብሔር ፍትሕ ገለጠ። (የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ነገረ መለኮት መዝገበ ቃላት፣ ገጽ 181-184 እና 329 - DICTIONARY OF BIBLICAL THEOLOGY, pp. 181-184 and 329) የመጨረሻው ፍትሕ በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ጊዜ ይመሠረታል። በዚያን ጊዜ በሌሎች ላይ ግፍና ክፋት የፈጸሙ ሁሉ እንደየሥራቸው ይቀጣሉ። ከዓመፅ ይልቅ ሰላምን በመምረጥ ሕይወታቸውን ያጡ የሐዋርያት፣ የቅዱሳን እና የሰማዕታት ደም - በአሁኑ ጊዜም የዋህነትን፣ ፍቅርን እና ራስን መሥዋዕት በማድረግ የእግዚአብሔርን ቃል ለመከተል የመረጡ ምእመናን ደም በከንቱ አልፈሰሰም፤ ፍትሕ ለሁሉምበመጨረሻው ፍርድ ይመለሳልና።

እኛ ስለ እምነታችን ከማንም በላይ እናውቃለን አንልም ይልቁንስ እኛ እግዚአብሔር ራሱ፣ ሐዋርያቱ እና ቅዱሳን በቀጥታ ያስተማሩንን እያስተጋባን ነው

ወንድሞች እና እኅቶች፣ የመጨረሻዋ ህቅታ እስትንፋሳችንን ስንተነፍስ ሁላችንም በምድር ላይ ስለአደረግነው ዓላማችን እና ተግባራችን መልስ እንድንሰጥ በእግዚአብሔር መላእክት እንጠየቃለን አሁን በተጠቀሰው መሠረት ወታደራዊ ጥቃትን በመደገፍ እና በማመፃደቅ ጉዳይ ላይ በአምላክ ፊት በልበ ሙሉነት ለመቆምና ተከራክረን ለማስረዳት ዝግጁ ነን?

ጊዜው ሳይዘገይ እውነቱን ለማየት አምላክ ለሁሉምልቡናውን ይግለጥለት። የዘለዓለም ሕይወት ለማግኘት ፍቅር ብቸኛው መንገድ ነው፤ ይሁን እንጂ ፍቅር በበቀል፣ ራስን በመጉዳት እና በጥላቻ እና ስሜቶች ከተበከለ ዘለዓለማዊሞትን ያመጣል

በአሁኑ ወቅት እውነተኛ ርኅራኄ እና እርዳታ ለሚሹት የትግራይ ሕዝብ ጨምሮ ለሁሉም ወንድሞቻችን፣ የዘለዓለም ሕይወት የሁሉም ምርጫ እንዲሆን እንጸልያለን

ይህንን ጽሑፍ ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች 13 4-13 በሰጠው የክርስቲያኖች ፍቅር ገለጻ ለመጨረስ ወደድንየተወሰደ፡-

ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤ የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል።

ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል። ከእውቀት ከፍለን እናውቃለንና፥ ከትንቢትም ከፍለን እንናገራለንና፤ ፍጹም የሆነ ሲመጣ ግን ተከፍሎ የነበረው ይሻራል።

ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፥ እንደ ልጅም አስብ ነበር፥ እንደ ልጅም እቈጥር ነበር፤ ጎልማሳ ሆኜ ግን የልጅነትን ጠባይ ሽሬአለሁ። ዛሬስ በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፤ ዛሬስ ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደ ታወቅሁ አውቃለሁ።

እንዲህም ከሆነ፥ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው።

(ዝግጅት በ: ሮ. ኢ.፣ ኃ. ገ. ፣ . ዮ.)