የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሰባት ስብከቶች ስለ ወንድ እና ሴት፡የትዳር ሕይወትና የትዳር ላይ ጥቃት
፠
ለኦርቶዶክስ ጋብቻ መመሪያ ፠
ይሄ ጽሑፍ የተወሰደው “ከሴቶች እኩልነት መብት ተከራካሪ ‘የጥርጣሬ ስብከት’ ባሻገር ከቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ወንድና ሴት ግንኙነት ትርጓሜ ፣ ትዳርና የትዳር ላይ ጥቃት ከኦርቶዶክስ አረዳድ አንጻር”
ከሚለው የሮሚና ኢስትራቲ ጽሑፍ ነው።
ዝግጅት በ: ሮ. ኢ.፣ ፍ. አ.፣ እ. ገ
4. የጥናት ዘዴ
ሁሉም ፎቶዎች እዚህ የመጡ ናቸው ፡፡
5. የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አስተምህሮዎች ዳሰሳ
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በትዳር ዙሪያ የሚያስተምረውን ትምህርት ጠንቅቆ ለማወቅ አስቀድመን የአዳም እና ሔዋንን አፈጣጠር እና ባለመታዘዛቸው ምክንያት ያጋጠማቸውን ስደት ማጤን ይኖርብናል፡፡
በኦሪት ዘፍጥረት ላይ የሰጠውን ትርጓሜ ስንቃኘው ሴቷ ከወንዱ ጋር በተመሳሳይ ሁኔታ እና በተመሳሳይ ክብር ሆና መፈጠሯን አጽንኦት ይሰጠዋል፡፡[1] ወንድ እና ሴት አስቀድመው አንድ የመሆናቸውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርትም በተደጋጋሚ ያነሣል፡፡ የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ኤፌሶን ሰዎችን በተረጎመበት ድርሳኑ ላይም ይህንን ትምህርት ካጸና በኋላ[2] አዳም እንደርሱ ያለች ረዳት እንደተፈጠረችለት ሲያውቅ ‹‹አጥንቷ ከአጥንቴ›› እና ‹‹ሥጋዋ ከሥጋዬ›› ማለቱን ይነግረናል[3]፡፡ በተጨማሪም የሴት ልጅ ከወንድ መፈጠር ራሱን የቻለ የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑን እና ይህም ደግሞ አዳም በምንም ሁኔታ ከእርሱ የተለየች ፍጡር እንደሆነች አድርጎ እንዳያያት እንደሆነ ይገልጽልናል[4]፡፡
በጉዳዩ ላይ ያለውን ኦርቶዶክሳዊ አረዳድ በሚያጸና መልኩ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደሚነግረን ከሆነ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ከመጣሳቸው በፊት በሁለቱ መካከል የሥጋ ውሕደት እንዲፈጠር የሚያደርግ ጾታዊ መሳሳብ አልነበረም፤ አዳምና ሔዋንም እርስ በእርስ በመረዳዳት እና በመተሳሰብ ላይ ያጠነጠነ ግንኙነት ውስጥ ነበሩ፡፡ በድንግልና ሕይወት ዙሪያ በጻፈው ድርሳን ላይ አዳምና ሔዋን በገነት እያሉ እንደ ሕጻናት ንጹሓን ነበሩ፤ ከእግዚአብሔር ጋርም ቀጥተኛ ግንኙነት ስለነበራቸው በሕይወታቸው ደስተኛ ነበሩ ይላል[5]፡፡ ለእግዚአብሔር ባለመታዘዛቸው ምክንያት ግን በኃጢአት አደፉ፤ ይሄም የእርስ በእርስ ግንኙነታቸውን ቀየረው፡፡ የሴት ልጅም እግዚአብሔር ከአዳም ከወሰደው አጥንት በሠራት ጊዜ በተፈጥሮ ላይ የተሰጣትን እኩል መብት ያጣችው በዚህ ጊዜ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደሚነግረን ከሆነም ላለመታዘዛቸው ባደረገችው አስተዋጽኦ ምክንያት በባሏ ላይ ጥገኛ እንድትሆን ተደርጋለች[6]፡፡ ሆኖም ግን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይህ የተደረገው እንደ ቅጣት ሳይሆን እንደ ስጦታ መሆኑን በመጥቀስ፤ ከውድቀታቸው በኋላ ሴቷ በብዙ ፍርሃት እና ችግር ውስጥ እንደምትገባ እግዚአብሔር በማወቁ እንደሆነ ያብራራልናል፡፡ ይህንን በተመለከተም እንዲህ ይለናል፡-
እዚህ ጋር የእግዚአብሔርን ምሕረት ተመልከቱ፡፡ “እርሱም ገዢሽ ይሆናል” የሚለውን ቃል በሰማች ጊዜ ትልቅ ሸክም እንደተጫነባት ማሰቧ አይቀርምና፤ ለዚህ ሲባል እግዚአብሔር የርሕራሄ ቃልን አስቀደመ፡፡ ይህንንም ያደረገው ‹‹ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል›› በማለት ነው፡፡ ይህም ደግሞ ማለት ‹‹እርሱ ከለላሽ እና መከታሽ ነው፤ በየቀኑ በምትኖሪው ሕይወትሽ ውስጥ እርሱ መከታ እና ከለላ ይሆንሻል፤ እኔም ወደ እርሱ ትሄጂ ዘንድ መብትን ሰጥቼሻለሁ›› ሲላት ነው፡፡ ይህንን መፍቀድ ብቻ ሳይሆን በጾታዊ ስሜትም ሁለቱን አስተሳስሯቸዋል፡፡ ኃጢያት ሴቲቱ ፈቃዷ ወደ ባሏ እንዲሆን እንዳደረገ፤ ሆኖም ግን አምላክ በቸርነቱ ይህንን ለእኛ መልካም ነገርን ለማድረግ እንዴት አድርጎ እንደተጠቀመበት ተመለከታችሁን?[7]
የሴቷ ከሥልጣን እርከን መውረድ ከገነት ስትወጣ ሊያስከትልባት ከሚችለው ፍርሃት እና ጉዳት ለመጠበቅ ሲል አምላክ በአዳም እና በሔዋን መካከል ጾታዊ መሳሳብን አደረገ፡፡ በዚህም ሥርዓት ምክንያት ባል የሚስት ራስ የተደረገው ለእርሷ ከለላ እንዲሆናት ሲሆን እርሷ፣ እግዚአብሔር ደግሞ በተፈጥሮ ሴቷ ወደ ወንዱ እንድትሳብ፣ እርሱም በተፈጥሮ እርሷን እንዲፈልጋት አድርጓል፡፡ የዚህም ምክንያት ግንኙነታቸው የፍቅር እና የመተማመን እንጂ ፍራቻ የነገሠበት እንዳይሆን በሚል ነው፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ የሰው ልጅ ወደ ኃጢያት ለማዘንበል ካለው ፍላጎት እና ከውድቀት በኋላም ሰይጣን የሰውን ልጅ ድኅነት ለማደናቀፍ ከሚያደርገው ከፍተኛ ሙከራ አንጻር ነው፡፡
እዚህ ጋር የሔዋን ከአዳም በታች የመሆን ጉዳይ እርሷ ሰፊ የሆነ ድርሻን ከተጫወተችበት ከመጀመሪያው በደል ጋር የሚገናኝ ሲሆን እርሱ ግን እርሷን ብቻ የሚያስጠይቅ አይደለም፡፡ በዚህ ረገድ እንዲያውም፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አዳምን እኩል ተጠያቂ ያደረገ ሲሆን፤ ስለአዳም በደል ምክንያት ባይሆን ኖሮ የሰው ልጅ ድኅነት ፈላጊ ባልሆነም ነበር[8]፡፡ በሌላ ጊዜ ደግሞ ‹‹የመጀመሪያው ሰው በደል››[9] በማለት ሲጽፍ እናነባለን፡፡ ይህ አካሄዱ በኦርቶዶክሳዊ አስተሳሰብ የተቃኘ መሆኑን የምናውቀውም፤ ጣት ከመጠቆም ይልቅ የተሰራው በደል የሚካስበት መንገድ ላይ ያተኮረ መሆኑን ስንገነዘብ ነው፡፡
የሔዋን መፈጠር ፡፡ ምስል ከግሪክ ኦርቶዶክስ ድር ጣቢያ ፡፡
በኦርቶዶክሳዊ ትውፊት መሠረት፤ ከሰው ልጅ ውድቀት በኋላ ድኅነትን ለማግኘት ሁለት አማራጮች አሉ፡- የመጀመሪያው በድንግልና የምናኔ ሕይወት መኖር ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ በጋብቻ ነው፡፡ ሁለቱም መንገዶች በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀባይነት ያላቸው ሲሆኑ በተለያዩ ዘመናት እነዚህን መንገዶች ለማጣጣል ከተነሱ መናፍቃን ቤተክርስቲያን ጠብቃናለች፡፡ ሆኖም ግን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የድንግልና ምናኔ ሕይወት ከጋብቻ ሕይወት እንደሚበልጥ ያምን ነበር፤ ለዚህም ደግሞ ምክንያቶች ነበሩት፡፡ ይህም በወንድ እና በሴት መካከል ያለው ጾታዊ መሳሳብ የሰው ልጅ ውድቀት ውጤት[10] መሆኑን እና አስፈላጊም የሆነውም በሰው ልጅ ድካም[11] ምክንያት መሆኑን በመጥቀስ ነው፡፡ የድንግልና ሕይይወት ግን ከሰው ልጅ ውድቀት በፊትም በመላእክት ዘንድ ሳይቀር ነበር[12]፡፡ በመሆኑም፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደሚነግረን ከሆነ፣ አንድ ሰው ወደ ሰማያዊ ሕይወት የበለጠ ለመቅረብ ከፈለገ የድንግልና ሕይወትን ይኖራል፡፡
በተጨማሪም በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትርጓሜዎች ላይ የድንግልና ሕይወት በትዳር ሕይወት ውስጥ ከሚገኙ ዓለማዊ ሃሳቦች የነጻ መሆኑ ተጽፏል፡፡ በምናኔ ሕይወት ውስጥ አንድ ሰው ሙሉ ለሙሉ ራሱን ለመንፈሳዊ ተግባራት በመስጠት እና ለነፍስ ድኅነት በመታገል መኖር የሚችል ሲሆን፤ በጋብቻ ሕይወት ውስጥ ግን ባለትዳሮች በዓለማዊ ጉዳዮች ውስጥ መግባት እና ለራሳቸውም ሆነ ለቤተሰብ አባላቶቻቸው ዓለማዊ እና መንፈሳዊ ሕይወት መጨነቅ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም፣ አንድ ትዳር መንፈሳዊ እንዲሆን ከተፈለገ በጋብቻ ውስጥ ያሉት አካላት እንዳልተጋቡ ሆነው መኖር አለባቸው - ይህም የቅዱስ ጳውሎስን ‹‹ሚስቶች ያሏቸው እንደ ሌላቸው ይሁኑ››[13] የሚለውን ቃል የሚያስተጋባ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ይህንን ተንተርሶ እንዲህ ብሎ ይጠይቃል፡- ‹‹ከወሰድነው በኋላ እንዳልወሰድነው የምንሆን ከሆነ መውሰድ ስለምን ያስፈልጋል;››[14]
በተጨማሪም ቅዱስ ዮሐንስ እንደሚነግረን ከሆነ ጋብቻን መረዳት ያለብን ወንዶች እና ሴቶች ኃጢያትን አሸንፈው ቅድስናን ገንዘብ ሊያደርጉ እንደሚችሉበት ምሥጢር ነው፡፡ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከውድቀት በኋላ በሰው ዘንድ ከፍተኛ ፈተና የሆኑትን እና ከእግዚአብሔር ጋር የሚደረገውን ኅብረትም ከሚከለክሉ ኃጢያቶች፣ ማለትም ከዝሙት እና ገላን ከመቸርቸር ራስን ለመጠበቅ ትዳር ጠቃሚ መሆኑን ትመክራለች፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ግን የትዳር ዓላማ በሰዎች ዘንድ ዘውትር በዚህ መልኩ ጥንቅቅ ተደርጎ እንደማይቀመጥ እና ብዙ ትኩረት የሚሰጠው የትዳር ዓላማም ልጅ መውለድ እንደሆነ ይገልጻል፡፡[15]
ከሰው ልጅ ውድቀት በኋላ ዘርን ማስቀጠል እና ለሰው ልጅ ድኅነት የተዘጋጀው እቅድም እንዲፈጸም ማድረግ ይገባ ነበር፡፡ ሆኖም ግን እግዚአብሔር ትዳርን የሰጠበት ዋነኛው ምክንያት የሰው ልጅ ኃጢያትን እንዳያሸንፍ እንቅፋት የሆኑትን ያልተገቡ ፍላጎቶች ማስወገድ ነበር[16]፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይህንን ለማጠየቅ የሚያነሣው ብዙዉን ዘመናቸውን ያለ ልጅ የኖሩትን አብርሃም እና ሳራን ነው፡፡ የአብርሃም እና የሳራ ጋብቻ ለአብርሃም የሚፈልገውን ልጅ የሚያገኝበት መንገድ ሊሆን እንዳልቻለ[17] በመጠቆም፤ ይህም ደግሞ ሰዎች ለመራባት ከፈለጉ ይህንን የሚያደርጉት በራሳቸው ጾታዊ ስሜት በኩል ወይንም በትዳር ስለታቀፉ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር ‹‹ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት›› የሚለው ሲታከልበት መሆኑን እንዲገነዘብ አድርጎታል፡፡ በሌላ አገላለጽ ቅዱስ ዮሐንስ እንደሚነግረን ከሆነ እግዚአብሔር ትዳርን ሲሰጥ ዋና ዓላማው ልጅ መውለድ ቢሆን ኖሮ ታላቅ ምስጢር የሆነውን ትዳር [በቤተክርስቲያን ውስጥ] መመስረት ባላስፈለገው ነበር፡፡ በመሆኑም የትዳር ዋና ዓላም ከዚህ እጅግ የላቁ ነው፡፡ ይህም ደግሞ ልክ ማጣትን፣ ቅምጥልነትን እና ራስን ማጉደፍ ከመሰሉ ኃጢያቶች ለመራቅም ነው፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በወንድ እና በሴት መካከል ያለው ኦርቶዶክሳዊ ኅብረት ታላቅ ምስጢር እንደሆነና፤ ይህም ኅብረት ከእግዚብሔር የተሰጠ መሆኑን ይነግረናል[18]፡፡ ወንድ ልጅ ያሳደጉትን አባት እና እናቱን ትቶ ወደማያውቃት ሴት ዘንድ እንዲሄድ መታዘዙ የትዳር ምሥጢር ምን ያህል ጥልቅ እንደሆነ ጠቋሚ አድርጎም ይወስደዋል[19]፡፡ በሁለቱ ተጋቢዎች መካከል ያለውም ጾታዊ መፈላለግ የዚህ ምስጢር አንድ ክፍል ሲሆን እንዲህ በማለትም ይጠቅሰዋል፡-
እነዚህ አንድ አካል ይሆናሉ፡፡ ይህ የፍቅር ምስጢር ነው፡፡ እነዚህ ሁለቱ አንድ
አካል ባይሆኑና ለየብቻቸው ቢኖሩ ልጆች ሊኖሯቸው
አይችሉም፤ አንድ አካል ወደ መሆን ሲዋሐዱ ግን ልጆችን ይወልዳሉ፡፡ ከዚህ ምን መማር እንችላለን? የዚህ
ግንኙነት ጥንካሬ ታላቅ ኋይል እንዳለው እንማራለን፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ገና ከፍጥረት ጅማሮ አንዱን ሁለት
አድርጎ ከፈለ፣ ለየብቻቸውም በራሳቸው መራባት እንደማይችሉ ለማሳየት ለብቻቸው ልጆችን ለመውለድ በቂ እንዳይሆኑ
አደረጋቸው፡፡ አንድ ሳይሆኑ ለየብቻቸው ግማሽ ናቸውና ልክ እንደ ጥንተ-ተፈጥሮው ጊዜ ሁሉ ልጆችን መውለድ
አይቻላቸውም[20]፡፡
አዳም እና ሔዋን አስቀድመው አንድ እንደነበሩት ሁሉ በትዳር ውስጥ ባል እና ሚስት አንድ ይሆናሉ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደሚነግረን ከሆነ ባል እና ሚስት በትዳር ከተዋሐዱ በኋላ ሁለት አካል ሳይሆኑ ቀድመው እንደነበሩት አዳም እና ሔዋን ሁሉ አንድ አካል ናቸው[21]፡፡ እንደገናም ሴቷን ‹‹ረዳት›› ብሎ መጥራቱ (ዘፍ 2፡18-20) አንድ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው ይላል[22]፡፡
አስቀድሞ የተገለጸውን ነጥብ ስንረዳ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ልጅን ስለመውለድ የተናገረውን ይዘን ኦሮቶዶክሳዊ ጋብቻ የሚያጠነጥነው ዘር በመተካት ላይ ብቻ እንደሆነ አድርገን ልንረዳ አይገባም፡፡ልጆች ለመተካት ሁለቱም (ባልና ሚስት) ማስፈለጋቸው በመካከላቸው ያለው የጥልቅ ትስስራቸው ከፍተኛ መገለጫ ብቻ ነው፡፡ የዚህን ትስስር ጥንካሬንም እንዲህ ሲል ጠቅሶታል፡-
መዝሙረኛው ዳዊት እጅግ በሚወደው በዮናታን ሞት ምክንያት ሐዘኑን ሲገልጽ የፍቅራቸውን ኃያልነት ለማሣየት የተጠቀመው ቃል ምን ነበር? ‹‹…ከሴት ፍቅር ይልቅ ፍቅርህ ለእኔ ግሩም ነበር›› [1 ሳሙ 1፡26] የሚል ነው፡፡ በወንድ እና በሴት መካከል ያለው ፍቅር ከስሜቶች ሁሉ ኃያል ነው፡፡ ሌሎች ስሜቶች ምንም ኃያል ቢሆኑም ስንኳ ይህ ስሜት ግን ከሌሎች በተለየ መልኩ የማይጠፋ ጽኑ እና በሁለቱ የተቃራኒ ጾታዎች ውስጥ በጥልቀት የተተከለ ነው፡፡ እኛ ልብ ባንለው ስንኳ ከመካከላችን ሆኖ ወንዶችን እና ሴቶችን አንዳቸውን ወደ አንዳቸው ይስባል - የዚህም ምክንያት በመጀመሪያ ሴት ከወንድ በመገኘቷ እና ከወንድ እና ከሴት ደግሞ ሌሎች ወንዶች እና ሴቶች ስለሚገኙ ነው[23]፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በወንድና በሴት መካከል ያለው የፍቅር ኃይል የተመሰለው አዳም የገዛ አካሉ ከሆነችው ከሔዋን ጋር እንዲዋሐድ ከመሰጠቱ ጋር መሆኑን ያብራራል(ዘፍ 3፡24)[24]፡፡ ይህ ከመጀመርያ ጀምሮ የነበረ አንድነት የተነሣው በሁለት ቀድሞ በማይገናኙ (አንድ ባልነበሩ) ወንድና ሴት መካከል ያለውን የተቃራኒ ጾታ ፍቅር ጥንካሬ ለማሳየት ነው፡፡የዚህ በባልና ሚስት መካከል ያለ ፍቅርና አካላዊ ውሕደት መረበሽ ትዳሩን ሊበጠብጠው ይችላል፡፡ ይህም በተለየ ግልጽ የሚሆነው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ክርስቲያን ካልሆነ ሰውና ዘማዊ ከሆነ ሰው ጋር የመጋባት ውጤት ምን እንደሚመስል በማነጻጸር ያስቀመጠውን ስንመለከት ነው፡፡ አንድ ሰው ክርስቲያን ያልሆነ ሰውን ቢያገባ ትዳሩን አይፍታ ምክንያቱም የአንዳቸው ክርስትና ሌላኛውን ይቀድሰዋልና ፤ ዘማዊ የሆነ ሰው ያገባ እንደሆነ ግን ትዳሩን ሊያጠፋው (ሊያፈርሰው) ይችላል ይላል[25]፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይሄንን ያለው በእንደዚህ ዓይነት ሕይወት ውስጥ ያሉ ሰዎችን ለማውገዝ አይደለም፤ ምክንያቱም በጸጸት ከተመለሱ ንስሓ የትኛውንም ኃጢአት ይቅር ያስብላልና ፤ ነገር ግን እንዲህ ማለቱ የጋብቻ ትስስር ጥንካሬ ወይም ኃይል ያለው በትዳሩ የአካላዊ ውሕደት ጥንካሬ ላይ መሆኑን ለማጠየቅ ነው፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የባለ ትዳሮች ውሕደት በቤተክርስቲያን በኩል መሆን እንዳለበትም በአጽንኦት ይናገራል፡፡ ይህንንም በተመለከተ ‹‹በሥጋዊ ፍላጎት ወይም በአንዳቸው አስገዳጅነት ሳይሆን በክርስቶስ የሆነ መንፈሳዊ ጋብቻ ትክክለኛ ጋብቻና መንፈሳዊ ልደት ነው፡፡››[26] ይላል፡፡ ጋብቻን መንፈሳዊ ልምምድ ለማድረግ ጋብቻው ወደ ድኅነት የሚወስድ ምሥጢረ ቤተክርስቲያን መሆኑን መረዳትና ከትዳር አጋር ጋር ከእግዚአብሔር በተሰጠ ሓላፊነት ድኅነቱን ገንዘብ ለማድረግ በጋራ አብሮ መኖር መሆኑን አምኖ መቅረብ ያስፈልጋል ፡፡ በወንጌል ትርጓሜው ላይ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ትዳር ግዴታዎች በዝርዝር ሲያብራራ በዋናነት በቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ ሚስቶች ሆይ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤ ክርስቶስ ደግሞ የቤተክርስቲያን ራስ እንደሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና››[27] በሚለው ትዕዛዝ ላይ በመንተራስ ነው፡፡(ኤፌ 5፡22-23) ከዚህ ጥቅስ በመነሣት ሚስቶች ለባሎቻቸው ልክ ቤተክርስቲያን ራሷ ለሆነው ለክርስቶስ የምታሳየውን ዓይነት ቅዱስ የሆነ ፍራቻና አክብሮት እንዲያሳዩ መጠየቃቸውን (ጠ ጠብቆ ይነበብ) ያብራራል፡፡ በኦርቶዶክስ አስተምህሮ ይሄ ፍራቻ ዓለማዊ ከሆነ በዛቻ ከሚመጣ ወይም አንድ ሰው በኃጢአቱ ወይም በጥፋቱ ምክንያት ከሚመጣበት ፍራቻ ፍጹም የተለየ ከፍቅር ጋር ብቻ የተሳሰረ የፍቅር ፍራቻ ነው፡፡[28] የፔንታፖሊሱ (አምስቱ ከተሞች) ሊቅ ኔክታርዮስ እንዳለው ‹‹ይሄ ፍራቻ እንደ ስሜትነቱ ከፍቅር ጋር የተሳሰረሲሆን በሴቷ ነፍስ ውስጥ የባል አክብሮትን የሚፈጥርና ካላቸው ጥብቅ ቁርኝት የተነሣ ባሏን ወደ አለማክበር ደረጃ እንዳትደርስ የሚጠብቃት ነው፡፡››[29]
ይሄን ዐሳብ የበለጠ ለማጠንከር ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በትዳር ውስጥ የባልን ሓላፊነት ያስረዳበትን በቅርበት (በአጽንኦት) መመልከት ጠቃሚ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሚስት ባሏን ታክብር ከሚለው ሓላፊነት በበለጠ የወንድ ሓላፊነት ጥልቅና ከባድ ነው ይላል፡፡
ምሳሌውን ገና አልጨረሰምና አሁን ደግሞ ካንተ ምን ሌላ ነገር እንደሚፈልግ ስማ ‹‹ባሎች ሆይ ክርስቶስ ደግሞ ቤተክርስቲያንን እንደወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ›› ብሏልና፡፡(ኤፌ 5፡25-26) ቀደም ብለን በሴቶች በኩል የሚፈለገውን የአክብሮት መጠን አይተናል፤ አሁን ደግሞ ስለ ፍቅር መጠን ስማ፡፡ ልክ ቤተክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛለት ሚስትህ ላንተ እንድትገዛልህ ትፈልጋለህ? እንግዲያውስ ልክ ክርስቶስ ለቤተክርስቲያን እንደሚያደርገው ሁሉ አንተም ሚስትህን ለመውደድና ለመንከባከብ ሓላፊነቱን መውሰድ አለብህ፡፡ ስለ ሚስትህ ስትል ማንኛውንም ዓይነት ስቃይና መከራ ሞትም ቢሆን ለመቀበል አታቅማማ፡፡ ይሄን ሁሉ አድርገህም ግን ክርስቶስ ለቤተክርስቲያን ያደረገላትን ያከል ለሚስትህ ልታደርግላት አትችልም፡፡[30]
ይሄ ዐሳብ በድጋሚ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ወንድ ራስነት ባብራራበት የኤፌሶን መልእክት ትርጓሜ ላይ ተነሥቷል፡፡ሰባኪው እዚህም ጋር በድጋሚ በትዳር ውስጥ በወንድና በሴት መካከል ያለውን ግንኙነት በክርስቶስና በቤተክርስቲያን መካከል ባለው ግንኙነት ምሳሌ ያስረዳል[31]፡፡ክርስቶስ ለቤተክርስቲያን ነፍሱን በፈቃዱ አሳልፎ እንደሰጣት ሁሉ ባልም የትዳር አጋሩ እንድትሆን ለመረጣት ለሚስቱ ይሄንን በጥቂቱ ስንኳ ሊያደርግላት ይገባል[32]፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በድጋሚ እንዲህ ይላል፡- “ሕይወትህን ስንኳ ለሚስትህ አሳልፈህ መስጠትህ አስፈልጊ ቢሆን፣ ዐሥር ሺ ጊዜ መቆራረጥ ቢኖርብህ፣ የትኛውንም ዓይነት ስቃይና መከራ መቋቋም ቢጠበቅብህ ወደኋላ አትበል፡፡ ይሄን ሁሉ አድርገህም ክርስቶስ ለቤተክርስቲያን ያደረገላትን ጥቂቱን ስንኳ ልታደርግ አትችልምና[33]፡፡”
በሌላ አገላለጽ ባል በትዳር ላይ የተሰጠው ራስነት ለሚስቱ ፍቅርና እንክብካቤ ካልሰጠ ሊሟላ አይችልም፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በእርሱ ዘመን ወንድ የበላይ በሆነበት ማኅበረሰብ ውስጥ አንደነበረው ልማድ ወንድ ይሄን በትዳር ላይ ያለውን የራስነት ሥልጣን አለአግባብ ባይጠቀምና ለሚስቱ ፍቅርና እንክብካቤ ቢቸር የሚያገኘው የተለየ ጥቅም ምንድነው? ለሚለው ጥያቄ ሲመልስ ባልና ሚስት ከትዳር በኋላ ለሚኖራቸው አንድ አካል[34] ባል ራስ ሲሆን ሚስት ደግሞ አካል ናት፤ ባል (ራስ) አካሉን (ሚስትን) ከጠላ አብሮ ይጠፋል[35] ምክንያቱም ራስ ያለ አካል ሊኖር አይችልምና፡፡ስለዚህ እንዲህ ብሎ ይመክራል፡-“ባል ሚስት ለምታሳየው አክብሮት ተመጣጣኝ የሆነ ፍቅር ይስጣት[36]፡፡”
ምንም ስንኳ ባሎች ለሚስቶቻቸው ተንከባካቢና በመንፈሳዊ ጉዳይ አስተማሪዎቻቸው እንዲሆኑ ቢጠይቅም የትዳር ግንኙነቱ ግን በሁለቱም እኩልነት ላይ የተመሠረት የሚስት ክብር ከባል ክብር ጋር በእኩል የሚታይበት መሆን እንዳለበት ያስተምራል[37]፡፡ ይሄንንም ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች የላከውን መልእክት በተረጎመበት ድርሳኑ አስረድቷል[38]፡፡ ሚስት ለባሏ ጌታም ባሪያም እንደሆነችው ሁሉ ባልም ለሚስቱ ጌታና ባሪያ ነው፡፡ ስለዚህ አንዳቸው በሌላኛው ላይ ራሳቸውን የበላይ አድርገው መመልከት የለባቸውም ፤ማናቸውም የበላይ ማናቸውም የበታች አይደሉም ፤ ይልቅስአንዳቸው በአንዳቸው ላይ የተመሠረቱ እኩል ባለሥልጣናት ናቸው፡፡ ይሄ አጽንኦት ሊሰጠው የሚገባ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ትዳር ውስጥ የሚገባ ሰው የትዳር አጋሩ አገልጋይ መሆን ስላለበት ደቀመዛሙርቱ ቢቻል ከማግባት እንዲከለከሉ የጻፈውን (1ኛ ቆሮ 7፡32-35) ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሲተረጉም እንዲ ብሏል፡-
በዚህ ቃል ቅዱስ ጳውሎስ ደቀመዛሙርቱን ከትዳር ሊያርቃቸው ይፈልጋል፡፡ ከትዳር በኋላ ለሚስትህ ፈቃድ የምትገዛ እንጂ የራስህ ጌታ እንደማትሆን ስታውቅ በዚህ ሓላፊነት (ትዳር) ውስጥ ላለማለፍ ትፈልጋለህ ምክንያቱም አንዴ ወደ ትዳር ከገባህ እስከ መጨረሻው ሚስትህን ለማስደሰት ባሪያ መሆንህ ነውና፡፡[39]
ይሄ ማለት ምንም ስንኳ በሴትና በወንድ መካከል የሥልጣን ተዋረድ ልዩነት ቢኖርም ባል ለሚስቱ በማንኛውም ጉዳይ ላይ አገልጋይዋ ይሆናል ማለት ነው፡፡ የትዳራቸውን ክብርና አንዳቸው የአንዳቸውን ክብር ማስጠበቅ ላይ ደግሞ ሁለቱም እኩል ሓላፊነት አለባቸው፡፡ በተመሳሳይ ውሕደታቸውን ሊጎዳ በሚችለው በዝሙት ኃጢአት መውደቅ ሁለቱንም እኩል የሚያስገስጽ ነው[40]፡፡
ምንም ስንኳ ባልና ሚስት ከትዳር በኋላ የሚኖራቸው የአንዱ አካል ራስና አካል ተብለው ቢገለጹም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አንድም ቦታ ጾታዊ የሓላፊነት ክፍፍሎች መለኮታዊ ዕቅድ ናቸው አለማለቱ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ ሚስቶች ለባሎቻቸው ውሳኔ እንዲታመኑና በመንፈሳዊ ጉዳይ መሪዎቻቸው እንደመሆናቸው እንዲያከብሯቸው ቢታዘዙም የጾታ ክፍፍል ያለበት የሕይወት መንገድ በአስተምህሮ መልክ በኦርቶዶክሳዊ ትውፊት ውስጥ የለም፡፡ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሴቶችን ለቤት (ለጓዳ) ሥራዎች ሓላፊ እያደረገ የተናገረበት ቦታ ሲኖር በዛ መልክ ለተከፋፈለ ማኅበረሰብ እየተናገረ እንደሆነ መታወቅ አለበት፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በትርጓሜዎቹ በባለትዳሮች መካከል የሚኖረውን ጾታዊ ግንኙነት ሳይነካው አላለፈም፡፡ ኦርቶዶክሳዊውን ትውፊት በማንሣት ባልናሚስት በሚኖራቸው የተራክቦ ውሕደት አንድ ሥጋ እንደሚሆኑ ያስረዳል፡፡ በተራክቦ ወቅት ሴቷ የወንዱን ዘር ትቀበልናበፍቅር መግባ ልጅ ታስገኛለች[41]፡፡ የሚወለደው ልጅ ደግሞ በወላጆቹ መካከል ድልድይ ይሆናል፤ አንድነቱንም ያጠነክራል፡፡ እዚህ ጋር ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የባልና የሚስትን አካላዊ ውሕደት ከአማኞች በሥጋ ወደሙ አማካኝነት ከክርስቶስ አካል ጋር ከመዋሐድ ጋር ያመሳስለዋል[42]፡፡ ይሄ አገላለጽ ግን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በትዳር ውስጥ ያለ ተራክቦ ልጅ ለመውለድ ብቻ የሚደረግ ነው ማለቱ እንዳልሆነ፤ ይልቅስ ልጅ በባለትዳሮቹ መካከል ያለ የፍቅር ግንኙነት ፍሬ መሆኑን ለማጠየቅ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የሕይወትን እውነታዎች ያለማፈር በግልጽ ያስቀምጥ ነበር፡፡ የጋብቻ መኝታው ክቡርና ቅዱስ መሆኑን በማስረዳት ከጾታዊ (ከተራክቦ) ውይይት የሚሸሹ ምእመናንን ይወቅስም ነበር፡፡ በጋብቻ የሚደረግ ተራክቦ አለአግባብ ማኅበራዊ ሥነ ምግባሮችን በጣሰ መንገድ እስካልተደረገ ድረስ ነውር የለበትም ይላል፡፡ ከዚህም ትዳር መንፈሳዊ የጋራ ጉዞ እንጂ በራሱ መድረሻ ወይም መጨረሻ አለመሆኑን በማሰብ የሚከናወን መሆን አለበት ማለቱን እንጂ በትዳር ውስጥ ያለን ተራክቦ አለመቃወሙን እንመለከታለን፡፡ ትዳር መንፈሳዊ ዓላማውን እንዲያሳካ ክርስቶስን ራስ ያደረገ የሁለት ሰዎች (የወንድና የሴት) መንፈሳዊ ትስስር መሆን አለበትና፡፡
በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት የትዳር መኝታው ክቡር ሲሆን አንዱ ዓላማውም ባለትዳሮቹ ከፍትወትና ከዝሙት ፈተና ራሳቸውን እንዲጠብቁ ማገዝ ነው፡፡ስለዚህም ምክንያት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ያለ ጋራ ስምምነት ከተራክቦ የሚታቀቡ ባለ ትዳሮችን ይቃወማል[43]፡፡ እንደርሱ ከሆነ ባለትዳሮች ከተራክቦ መታቀብ ያለባቸው ሁለቱም በጾምና በጸሎት በተአቅቦ ለመቆየት ከተስማሙ ብቻ መሆን አለበት (ጾምና ጸሎቱን ግን ተራክቦን ባላቋረጡም ጊዜ መቀጠል አለባቸው)፡፡ በሁለቱም ፈቃድ የሚደረግ ካልሆነ ግን ፈቃደኛ ያልሆነውን አጋር ለዝሙትና ሌሎች ፈተናዎች ሊያጋልጠው ይችላል፤ ይሄ ደግሞ ለመንፈሳዊ ዕድገትና ቅድስና በጋራ የጀመሩትን ሕይወት(ጉዞ) ማደናቀፍ ነው፡፡
ትዳር በሁለት ፍቅረኛሞች መካከል በጋራ እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚፈጸም ኅብረት ቢሆንም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ካስተዋላቸው ልምዶች በመነሣት የትዳር ሕይወት ሁሌ ሰላማዊ ላይሆን እንደሚችልና ባለትዳሮቹም ራስ ወዳድ የሚሆኑበት አጋጣሚ ሊኖር እንደሚችል ይናገራል፡፡ ስለ ድንግልና ባብራራበት የወንጌል ትርጓሜው ትዳር እጅግ መታገስና መቻቻልን ይሻል ይላል[44]፡፡ በአንድ አጋጣሚ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምእመናንን እንዲህ ብሎ ጠየቃቸው ‹‹ባል ለዘብተኛ ቢሆንና ሚስት ግን ተንኮለኛ ፣ ስም አጥፊ፣ ወረኛ፣ ቅንጡ…ወዘተ ብትሆንስ ? በተቃራኒው ደግሞ ሚስት ጭምትና መልካም ሆና ባል ደግሞ ነውረኛ ግድ የለሽ ፣ የማያስተውል ፣ ትዕቢተኛ ፣ ግልፍተኛ፣ ቁስ ወዳጅና ተማቺ ቢሆንስ?[45] ይሄንን ጥያቄ ሲመልስ አንዳቸው የአንዳቸውን ድክመት ለመሸከም መሞከር እንዳለባቸውና መጥፎ ጸባያቸውን እንዲያርሙ በመምከርና በማገዝ ጥሩ መንፈሳዊ ሰው ሊያደርጓቸው እንደሚገባ ቅዱስ ጳውሎስ ያስተማረውን በመድገም ነው፡፡ ከዚህ ነጻ የሚሆኑትም አንዳቸው በሞት ሲለዩ ብቻ ነው ይላል፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በትዳር ውስጥ ትዕግሥትና መቻቻል ኦርቶዶክሳዊ ጸባይ መሆናቸውን ሲያነሣ ያለ ጾታዊ ልዩነትለሁለቱም ጾታዎች እያለ መሆኑ ሊሠመርበት ይገባል[46]፡፡ በትዳር ውስጥ ያለ የትዳር ጥቃት (በዚሁ ጽሑፍ ይሄን ቃል የተጠቀምነው በትዳር ውስጥ የሚፈጸምን ጥቃት ሁሉ ለማመልከት ነው) ኢ-ኦርቶዶክሳዊ ስለሆነ ሲያወግዝም ደግሞ ሁለቱንም እንደሚመለከት በመጠቆም ነው፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው ሚስቶች ባሎቻቸውን በድህነት ምክንያት እንዳይወቅሱ ወይም እንዳይሰድቡ[47]፤ ባሎችም በሚስቶቻቸው መከበርን በኃይልና በማስፈራራት ሳይሆን በፍቅርና በመልካም ጠባይ ለያገኙት እንደሚገባ[48] መምከሩ ነው፡፡ እንዲህ በማለት፡-
“… ባል ይሄንን ሲሰማ ሥልጣን ስላለው (የሚስቱ ራስ ስለሆነ) ሚስቱን መስደብና መጉዳት የለበትም ይልቅስ ለመልካም ነገር ሊያበረታታት ፣ ሊመክራትና ሊያግዛት ይገባል፤ እንደገናም በንግግር ሊያሳምናት እንጂ እጁን ሊያነሣባት አይገባም፡፡ እነዚህ ሁሉ አንድ መንፈሳዊ ከሆነ ሰው መራቅ ያለባቸው ሲሆኑ፤ ከኩራት፣ ከስድብ፣ ከማሸማቀቅና ከማቃለል ይልቅ መምከር፣ ማገዝና መርዳት አለበት፡፡”[49]
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ወንዶች መንፈሳዊ ሥልጣናቸውን አለአግባብ እንዳይጠቀሙ ያስጠነቅቃል ምክንያቱም በዓለም ትብታብ ካልታሰረና በሃይማኖት ከሚኖር ወንድ ይሄ የማይጠበቅ በመሆኑ ነው፡፡ ትክክለኛ ባል ቅንና ታጋሽ፣ ለሚስቱ ሲመልስላትም በጥንቃቄ በተሰደሩና መንፈሳዊ መረዳትን በሚጨምሩ መካሪ ቃላት መሆን አለበት፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሴቶችን ከጥቃት ለመጠበቅ ያለውን ጽኑ አቋም ያረጋገጠው ሚስቶች ምንም ስንኳ የሚያናድድና ለትችት የሚዳርግ ነገር ቢኖራቸውም ባሎች ታጋሽ፣ መልካምና ለፍርድ የማይቸኩሉ እንዲሆኑላቸው በማዘዙ ነው፡-
አንድ ሰው ባሪያውን በማስፈራራት ሊገዛው ይችል ይሆናል፤ አኔ ግን አይሆንም እላለሁ ምክያቱም ያ ባርያ አንድ ቀን ከታሰረበት ሰንሰለት አምልጦ ሊጠፋ ይችላል፡፡ እንግዲህ አንድ ሰው ባሪያውን ስንኳ በጉልበት መግዛት ካልቻለ የሕይወቱን አጋር ሚስቱን ፣ የልጆቹን እናት፣ የደስታውን ምንጭ በጉልበትና በማስፈራራት ሳይሆን በፍቅርና በደስታ ሊያኖራት ይገባል፡፡ ሚስት ባልን የምትፈራው ከሆነ ምን ዓይነት ትዳር ይኖራቸዋል? ባልስ እንደባርያ ከሚያኖራትና ነጻነት ከሌላት ሚስቱ ምን ዓይነት ደስታን ሊያገኝ ይችላል? ስለ እርሷ መከራ ቢደርስብህ ስንኳ ልትወቅሳት አይገባም ክርስቶስ በቤተክርስቲያን ላይ ይሄን አላደረገምና፡፡[50]
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አንድ ሰው በባርያው የሚፈራው መፈራትና ባል ነጻ ፈቃድ ባላት ሚስቱ የሚፈራው መፈራት መካከል ግልጽ የሆነ ልዩነት ያስቀምጣል፡፡ የሚስት ፍራቻ የአክብሮት ነው፡፡ ይሄም አክብሮት ባሏ ለእርሷ ከሚኖረው መልካም አመለካከት፣ ከሚናገራት መልካም ንግግሮች እና ከሚያሳያት መልካም አካላዊ ምላሾች የሚመነጭ ነው፡፡ ባል ሚስቱን ከመውቀስ ተከልክሎ ስለሚስቱ መከራን አንዲቀበል በዚህም ክርስቶስን አንዲመስል በትዳር ውስጥ ያለውን ኅብረት በቤተክርስቲያንና በክርስቶስ መካከል ባለው ኅብረት እየመሰለ ያሳስባል፡፡ ይሄንንም በተለያዩ ቦታዎች ላይ አጽንኦት ሰጥቶ ይሰብካል፡፡ እንዲህ አንዳለ ‹‹ሚስት አካልህ ስለሆነች ክፉ ነገሮች የምታደርግባት ከሆነ የራስህን አካል ባለማክበርህ ትዋረዳለህ (ታፍራለህ)››[51] በሌላም ቦታ እንዲህ አንዳለ ‹‹የራሱን አካል (ራሱን) የሚጠላ ሰው የለም››፡፡[52]
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አንዳንዴ የሚስቶች ጸባይ ከአቅም በላይ ቢሆን ስንኳ እንዲታገሷቸውና ሁሌም በመልካም መንገድ እንዲቀርቧቸው ለባሎች የተናገረ ብቻ አይደለም፡፡ ይህ ከእግዚብሔር የተሰጣቸው ሓላፊነት መሆኑን ጭምር እንጂ፤ እንዲህ አንዳለ ‹‹ስለ ማንነቷ ብለህ ከምትወዳት የበለጠ ስለ ክርስቶስ ብለህ ውደዳት››[53] በተመሳሳይም ፈርሃ እግዚአብሔር ያለው ባል ሚስቱን እንደሚወድ ባለ ፍቅር ባሎች ሚስቶቻቸውን ባይወዱ ስንኳ ሚስቶች ግን ባሎቻቸውን ከመውደድና ከማክበር አንዳይከለከሉ ያዛል፡፡[54] ይሄም በሁለቱም በኩል እጅግ አስፈላጊ ነው ምክንያቱም በትዳር ላይ ሳሉ ጉድለት ወይም መቀያየም ሊኖር ስለሚችል አንዳቸው በሌላኛቸው ላይ ባለመፍረድ በትዳር ሕይወታቸው ለእግዚአብሔር ያለባቸውን ሓላፊነት ሟሟላት ላይ ማተኮርአለባቸውና ነው፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ባልና ሚስት አብረው መቀጠል በፍጹም የማይችሉ እንደሆነ በይሉኝታ ታስረው ከመቆየት ቢለያዩ አንደሚመርጥም አንዲህ በማለት ያስረዳል፡-
ላገቡ ሰዎች ክርስቶስ ያዘዘው ነገር ምንድነው? ሚስት ከባሏ እንዳትለይ ከተለየች ግን ሳታገባ እንድትኖር ወይም ከባሏ አንድትታረቅ ነው፡፡፡ በተራክቦ ካለመስማማት እና በሌሎች ተራ ምክንያቶች እንደገናም አንዳቸው ለአንዳቸው ክፉ ከመሆን የተነሣ ትዳሮች ይፈርሳሉ፤ እንዲህ ዓይነት ነገር ባይፈጠር መልካም ነው ከተፈጠረ ግን ሴቷ ሌላ ባል አንዳይኖራት ትዳሩ ፈርሶም ቢሆን በአንድ ቤት አብራው ባትኖርም ስንኳ ባሏን ሳትፈታ ትኑር ፡፡[55]
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መለያየትን ላለማበረታታት ይጥራል ምክንያቱም እግዚአብሔር አንድ ያደረጋቸውን ሁለቱን ክፋዮች መለያየት አግባብ አይደለምና፡፡ ነገር ግን አብሮነታቸው በሁለቱ መካከል ጠላትነትን እየጨመረ የሚሄድ ከሆነ ተለያይተው ቢኖሩ ይመርጣል፡፡ ይሄን ሲያደርጉ ግን ወደፊት ለመታረቅ በር ይከፈት ዘንድ ሳያገቡ መቆየት አንዳለባቸው ይመክራል፡፡[56] ይሄን የመከረው ግን እርሱ ገንዘብ ካደረገው ኦርቶዶክሳዊ አረዳድ በመነሣት አንጂ ሁሉን የሚገዛ ሕግ ለመሥራት እንዳይደለ መታወቅ አለበት፡፡
[1]
“πόσης εὐφροσύνης αὐτοῦ ἡ ψυχὴ ἐνεπίμπλατο κοινωνὸν θεωρῶν τὴν γυναῖκα, καὶ
ὁμότροπον καὶ ὁμόδοξον αὐτὴν καθεστῶσαν;” In Genesim (sermo 3).
[2]
“ὥσπερ καὶ ἡ Εὔα σὰρξ ἀπὸ τῆς σαρκὸς τοῦ Ἀδάµ.” In Epistulam ad
Ephesios, Homily 20.
[3]
“ Ἄκουε· Τοῦτο νῦν ὀστοῦν ἐκ τῶν ὀστῶν μου, φησὶ, καὶ σὰρξ ἐκ
τῆς σαρκός μου”. In Epistulam ad Ephesios, Homily 20.
[4]
አትኩሮቱን
የሚያደርገው ሥጋ (‘σαρκὸς’)
እና አጥንት
(‘ὀστῶν’)
ላይ ነው፡፡ ይህንንም ያደረገው
በሁሉም ረገድ ሴቷ ከወንዱ ጋር በአንድ አይነት ሁኔታ መፈጠሯን ለማጠየቅ ነው፡፡
[5]
“Πλασθεὶς δὲ ἐκεῖνος ἔμεινεν ἐν παραδείσῳ καὶ γάμου λόγος οὐδεὶς
ἦν.Ἐδέησεν αὐτῷ γενέσθαι καὶ βοηθόν, καὶ ἐγένετο, καὶ οὐδὲ οὕτως
ὁ γάμος ἀναγκαῖος εἶναι ἐδόκει.Ἀλλ' οὐδὲ ἐφαίνετό που, ἀλλ'
ἔμενον ἐκεῖνοι τούτου χωρὶς καθάπερ ἐν οὐρανῷ τῷ παραδείσῳ
διαιτώμενοι καὶ ἐντρυφῶντες τῇ πρὸς Θεὸν ὁμιλίᾳ.Μίξεως δὲ
ἐπιθυμία καὶ σύλληψις καὶ ὠδῖνες καὶ τόκοι καὶ πᾶν εἶδος φθορᾶς
ἐξώριστο τῆς ἐκείνων ψυχῆς.”In De virginitate, Paragraph
14.Translation in Miller,
Women, 109.
[6]
“Ἐποίησά σε, φησὶν, ὁμότιμον· οὐκ ἐχρήσω καλῶς τῇ ἀρχῇ· μετάβηθι
πρὸς τὴν ὑποταγήν.Οὐκ ἤνεγκας τὴν ἐλευθερίαν, κατάδεξαι τὴν
δουλείαν.Οὐκ οἶδας ἄρχειν, καὶ δι' αὐτῆς τῶν πραγμάτων ἔδειξας
τῆς πείρας· γενοῦ τῶν ἀρχομένων, καὶ τὸν ἄνδρα ἐπίγνωθι
κύριον.Πρὸς τὸν ἄνδρα σου ἡ ἀποστροφή σου, καὶ αὐτός σου
κυριεύσει.” In Genesim Sermones, Homily 4.Translation in Miller,
Women, 30.
[7]“Καὶ
ὅρα
Θεοῦ
ἐνταῦθα
φιλανθρωπίαν.
Ἵνα γὰρ
μὴ
ἀκούσασατὸ,
Αὐτός
σου
κυριεύσει,
φορτικὴν
εἶναι
νομίσῃ
τὴν
δεσποτείαν,
πρότεροντὸ τῆς
κηδεμονίας
ἔθηκεν ὄνομα
εἰπὼν,
Πρὸς
τὸν
ἄνδρα
σου ἡ
ἀποστροφή
σου,
τουτέστιν,
Ἡ
καταφυγή
σου καὶ
ὁ
λιμὴν
καὶ
ἡ ἀσφάλεια
ἐκεῖνος
ἔσται σοι·
ἐν
πᾶσι
τοῖς
ἐπιοῦσι δεινοῖς
πρὸς
ἐκεῖνον
ἀποστρέφεσθαι
καὶ καταφεύγειν
σοι
δίδωμι.
Οὐ
ταύτῃ
δὲμόνον,
ἀλλὰ
καὶ
φυσικαῖς
αὐτοὺς
συνέδησεν ἀνάγκαις
καθάπερ
ἄῤῥηκτόν τινα
δεσμὸν,
τὴν
ἐκ
τῆς
ἐπιθυμίας περιβαλὼν
αὐτοῖς
ἅλυσιν.
Εἶδες
πῶς
εἰσήγαγε
μὲν
τὴν ὑποταγὴν
ἡ
ἁμαρτία,
ὁ
δὲ
εὐμήχανος
καὶ
σοφὸς Θεὸς
καὶ
τούτοις
πρὸς
τὸ συμφέρον
ἡμῖν
ἀπεχρήσατο;”
In
Genesim
Sermones,
Homily
4. Original
translation
in
Miller,
Women, 30
with
underlined
alterations.
[8]“Ὥσπερ
οὖν τότε ἀπὸ νεκρῶν σωμάτων τοσαύταις μυριάσι δέδωκεν ὑπόθεσιν
καὶ ῥίζαν ὁ Θεός, οὕτω καὶ παρὰ τὴν ἀρχὴν εἰτοῖ ςπροστάγμασιν
αὐτοῦ πεισθέντες οἱ περὶ τὸν Ἀδὰμ τῆς ἡδονῆς ἐκράτησαν τοῦ ξύλου,
οὐ κἂν ἠπόρησεν ὁδοῦδι'ἧς τὸ τῶν ἀνθρώπων γένος αὐξήσει.”
De
Virginitate,
Paragraph
15. Translation
in
Miller,
Women, 110.
[9]
ለአብነት ያህል፡
Genesim
(sermo
3) ላይ
የመጀመሪያዎቹ
ሰዎች
“τὸν πρῶτον ἄνθρωπον”
ጾምን መጠበቅ
ስላቃታቸው
ገነትን
ማጣታቸውን
ይነገረናል፡፡
‘ἄνθρωπος’ (በግሪክ
ቋንቋ ‹ሰው›ማለት ነው)
የሚለው
ቃል
ምንጭ አከራካሪ
ቢሆንም፣
ብዙዉን ጊዜ
ግን
‘ἄνδρ-ωπος’
ከሚለው
ቃል ጋር
የሚገናኝ
ነው፤ እርሱም
ደግሞ
የሰው (ἀνήρ). መልክ
ያለውን
አንድ አካል
የሚጠቁም
ነው፡፡ ቅዱስ
ዮሐንስ
አፈወርቅ
‹ሰው›
እና
‹ወንድ›
የሚሉትን ቃላት
በመለያየት
ስለሚጠቀማቸው፤ እዚህ
ጋር
አዳምን ብቻ
ማለቱን
እንደሆነ ያጠራጥራል፡፡
ይህ
ቢሆንም ሔዋንን
ብቻ
ጥፋተኛ አድርጎ
አለመናገሩን
የሚደግፍልን መከራከሪያ
ነጥብ
ነው፡፡
[10]
“Ἀπὸ τῆς παρακοῆς, ἀπὸ τῆς ἀρᾶς, ἀπὸ τοῦ θανάτου. Ὅπου γὰρ
θάνατος, ἐκεῖ γάμος.” De Virginitate,
Paragraph 14.Translation in Miller,
Women, 109.
[11]
Original being “ἀσθένειαν.”
[12]
“Ἀλλ'
οὐχ
ἡ
παρθενία
ταύτην
ἔχει
τὴν
ἀκολουθίαν
ἀλλ'
ἀεὶ
χρήσιμον,
ἀεὶ
καλὸν
καὶ
μακάριον
καὶ
πρὸ
τοῦ
θανάτου
καὶ
μετὰ
τὸν
θάνατον
καὶ
πρὸ
τοῦ
γάμου
καὶ
μετὰ
τὸν
γάμον,”
De Virginitate, Paragraph 14.
[13]
1 ቆሮንጦስ 7፡29
[14]
“τί χρὴ λαβεῖν τοσοῦτον ὄγκον, ὅταν καὶ μετὰ τὸ λαβεῖν οὕτω δέοι
χρῆσθαι, ὡς μὴ ἔχοντα;”In Epistulam i ad Corinthios, Homily
19.Original translation from Schaff,
NPNF1-12, 194.
[15]
“Ὅτι
πάλαι
μὲν
τῷ
γάμῳ
δύο
προφάσεις,
νῦν
δὲ
μία.
Ἐδόθη
μὲν
οὖν
καὶ
παιδοποιΐας
ἕνεκεν
ὁ
γάμος·
πολλῷ
δὲ
πλέον
ὑπὲρ
τοῦ
σβέσαι
τὴν
τῆς
φύσεως
πύρωσιν.
Καὶ
μάρτυς
ὁ
Παῦλος
λέγων·
«∆ιὰ
δὲ
τὰς
πορνείας
ἕκαστος
τὴν
ἑαυτοῦ
γυναῖκα
ἐχέτω»,
οὐ
διὰ
τὰς
παιδοποιΐας.
Καὶ
πάλιν
ἐπὶ
τὸ
αὐτὸ
συνέρχεσθαι
κελεύει
οὐχ
ἵνα
πατέρες
γένωνται
παίδων
πολλῶν,
ἀλλὰ
τί;
«Ἵνα
μὴ
πειράζῃ
ὑμᾶς
ὁ
σατανᾶς»,
φησί.
Καὶ
προελθὼν
δὲ
οὐκ
εἶπεν·
εἰ
δὲ
ἐπιθυμοῦσι
παίδων,
ἀλλὰ
τί;
«Εἰ
δὲ
μὴ
ἐγκρατεύονται,
γαμησάτωσαν.»
Παρὰ
μὲν
γὰρ
τὴν
ἀρχήν,
ὅπερ
ἔφην,
δύο
ταύτας
εἶχε
τὰς
ὑποθέσεις·
ὕστερον
δὲ
πληρωθείσης
καὶ
τῆς
γῆς
καὶ
τῆς
θαλάττης
καὶ
τῆς
οἰκουμένης
πάσης
μία
λείπεται
πρόφασις
αὐτοῦ
μόνη,
ἡ
τῆς
ἀκολασίας
καὶ
ἡ
τῆς
ἀσελγείας
ἀναίρεσις.” De
Virginitate, Paragraph 19. Translation in Miller,
Women, 113.
[16]
Predicting that he could be blamed for denigrating the laws of
Moses, Chrysostom reassuredly explained:
“Κακίζω
μὲν
οὐδαμῶς·
Θεὸς
γὰρ
αὐτὰ
συνεχώρησε
καὶ
γέγονεν
ἐν
καιρῷ
χρήσιμα.
Μικρὰ
δὲ
αὐτὰ
εἶναί
φημι,
καὶ
παίδων
κατορθώματα
μᾶλλον
ἢ
ἀνδρῶν.
Καὶ
διὰ
τοῦτο
ἡμᾶς
τελείους
ὁ
Χριστὸς
δημιουργῆσαι
βουλόμενος
ἐκεῖνα
μὲν
ἀποθέσθαι
ἐκέλευσεν,
ὥσπερ
ἱμάτια
παιδικὰ
καὶ
οὐ
δυνάμενα
περιβάλλειν
τὸν
ἄνδρα
τὸν
τέλειον
οὐδὲ
τὸ
μέτρον
κοσμῆσαι
τῆς
ἡλικίας
τοῦ
πληρώματος
τοῦ
Χριστοῦ,
τὰ
δὲ
ἐκείνων
εὐπρεπέστερα
καὶ
τελειότερα
περιθέσθαι
ἐκέλευσεν,
οὐκ
ἀντινομοθετῶν
ἑαυτῷ
ἀλλὰ
καὶ
σφόδρα
ἀκολουθῶν.”
De Virginitate, Paragraph 16. Translation in Miller,
Women, 110-111.
[17]
“Καὶ νῦν δὲ οὐχ ἡ τοῦ γάμου δύναμις τὸ γένος συγκροτεῖ τὸ
ἡμέτερον ἀλλ' ὁ τοῦ κυρίου λόγος ὁ παρὰ τὴν ἀρχὴν εἰπών· «Αὐξάνεσθαι
καὶ πληθύνεσθαι καὶ πληρώσατε τὴν γῆν.” Τί γάρ, εἰπέ μοι, τὸν
Ἀβραὰμ εἰς παιδοποιΐαν τὸ πρᾶγμα ὤνησεν; Οὐκ ἐπὶ τοσούτοις αὐτῷ
χρησάμενος ἔτεσι ταύτην ὕστερον ἀφῆκε τὴν φωνήν· ‘∆έσποτα, τί
μοι δώσεις; Ἐγὼ δὲ ἀπολύομαι ἄτεκνος;’”De Virginitate, Paragraph
15. Translation in Miller, Women, 110.
[18]
“δεσµὸς ὡρισµένος παρὰ Θεοῦ.” In Epistulam ad Colossenses,
Homily 12.
[19]
“Ὄντως γὰρ, ὄντως μυστήριόν ἐστι, καὶ μέγα μυστήριον, ὅτι τὸν
φύντα, τὸν γεννησάμενον, τὸν ἀναθρεψάμενον, τὴν ὠδινήσασαν, τὴν
ταλαιπωρηθεῖσαν ἀφεὶς, τοὺς τὰ τοσαῦτα εὐεργετήσαντας, τοὺς ἐν
συνηθείᾳ γενομένους, τῇ μηδὲ ὀφθείσῃ, μηδὲ κοινόν τι ἐχούσῃ πρὸς
αὐτὸν προσκολλᾶται, καὶ πάντων αὐτὴν προτιμᾷ. Μυστήριον ὄντως
ἐστί.Καὶ οἱ γονεῖς τούτων γινομένων οὐκ ἄχθονται, ἀλλὰ μὴ
γινομένων μᾶλλον· καὶ χρημάτων ἀναλισκομένων καὶ δαπάνης
γινομένης, ἥδονται.” In Epistulam ad Ephesios, Homily 20.
[20]
“Ἔρχονται ἓν σῶμα γενησόμενοι.Ἰδοὺ πάλιν ἀγάπης μυστήριον.Ἂν οἱ
δύο µὴ γένωνται ἓν, οὐκ ἐργάζονται πολλοὺς, ἕως ἂν δύο µένωσιν·
ὅταν δὲ εἰς ἑνότητα ἔλθωσι, τότε ἐργάζονται.Τί µανθάνοµεν ἀπὸ
τούτου; Ὅτι πολλὴ τῆς ἑνώσεως ἡ ἰσχύς. Τὸ εὐµήχανον τοῦ Θεοῦ τὸν
ἕνα εἰς δύο διεῖλε παρὰ τὴν ἀρχὴν, καὶ θέλων δεῖξαι ὅτι µετὰ τὸ
διαιρεθῆναι καὶ εἷς µένει, οὐκ ἀφῆκεν ἕνα ἀρκεῖν πρὸς τὴν
γέννησιν. Οὐ γάρ ἐστιν εἷς [ὁ] οὐδέπω, ἀλλ' ἥµισυ τοῦ ἑνός· καὶ
δῆλον, ὅτι οὐ παιδοποιεῖ, καθάπερ καὶ πρότερον.”
InEpistulamadColossenses, Homily 12.Translation with reference
to the modern Greek in
Παιδαγωγική, p. 22
[21]
“Γυνὴ γὰρ καὶ ἀνὴρ οὐκ εἰσὶν ἄνθρωποι δύο, ἀλλ' ἄνθρωπος εἷς.”InEpistulam
ad Colossenses
[22]
“∆ιὰ τοῦτο καὶ βοηθὸν καλεῖ, ἵνα δείξῃ ὅτι ἕν εἰσι.”In Epistulam
ad Colossenses, Homily 12.
[23]
“∆ιὰ τοῦτο καί τις τὴν ὑπερβάλλουσαν ἀγάπην δηλῶν µακάριος ἀνὴρ,
καί τινα τῶν αὐτῷ φίλων καὶ ὁµοψύχων πενθῶν, οὐ πατέρα εἶπεν, οὐ
µητέρα, οὐ τέκνον, οὐκ ἀδελφὸν, οὐ φίλον, ἀλλὰ τί; Ἔπεσεν ἐπ'
ἐµὲ ἡ ἀγάπησίς σου, φησὶν, ὡς ἀγάπησις τῶν γυναικῶν.Ὄντως γὰρ,
ὄντως πάσης τυραννίδος αὕτη ἡ ἀγάπη τυραννικωτέρα.Αἱ μὲν γὰρ
ἄλλαι, σφοδραί· αὕτη δὲ ἡ ἐπιθυμία ἔχει καὶ τὸ σφοδρὸν, καὶ τὸ
ἀμάραντον.Ἔνεστι γάρ τις ἔρως ἐμφωλεύων τῇ φύσει, καὶ λανθάνων
ἡμᾶς συμπλέκει ταῦτα τὰ σώματα.∆ιὰ τοῦτο καὶ ἐξ ἀρχῆς ἀπὸ ἀνδρὸς
ἡ γυνὴ, καὶ μετὰ ταῦτα ἀπὸ ἀνδρὸς καὶ γυναικὸς ἀνὴρ καὶ γυνή.In
Epistulam ad Ephesios, Homily 20.Translation in Roth and
Anderson, St.John
Chrysostom, 43-44 with underlined alterations.
[24]
“Ὁρᾷς σύνδεσμον καὶ συμπλοκὴν, καὶ πῶς οὐκ ἀφῆκεν ἑτέραν
ἐπεισελθεῖν οὐσίαν ἔξωθεν; Καὶ ὅρα πόσα ᾠκονόμησε.Τὴν ἀδελφὴν
ἠνέσχετο γαμῆσαι αὐτὸν τὴν αὑτοῦ, μᾶλλον δὲ οὐ τὴν ἀδελφὴν, ἀλλὰ
τὴν θυγατέρα, μᾶλλον δὲ οὐ τὴν θυγατέρα, ἀλλά τι πλέον θυγατρὸς,
τὴν σάρκα τὴν αὑτοῦ.Τὸ δὲ ὅλον ἐποίησεν ἄνωθεν, ὥσπερ ἐπὶ τῶν
λίθων, εἰς ἓν αὐτοὺς συνάγων.” Translation in Roth and Anderson,
St. John Chrysostom, 43-44.
[25]
Πῶς γὰρ ἡ τὸν ἔμπροσθεν ἀτιμάσασα χρόνον, καὶ γενομένη ἑτέρου,
καὶ τοῦ γάμου τὰ δίκαια ἀφανίσασα, ἀνακαλέσασθαι δυνήσεται τὸν
ἠδικημένον, πρὸς τούτοις καὶ τὸν μένοντα ὡς ξένον; Πάλιν ἐκεῖ
μὲν μετὰ τὴν πορνείαν ὁ ἀνὴρ οὐκ ἔστιν ἀνήρ· ἐνταῦθα δὲ, κἂν
εἰδωλολάτρις ἡ γυνὴ, τοῦ ἀνδρὸς τὸ δίκαιον οὐκ ἀπόλλυται.”In
Epistulam i ad Corinthios, Homily 19.Translation in Schaff,
NPNF1-12, 189.
[26]
“Ἄρα γάμος ἐστὶν οὗτος γινόμενος κατὰ Χριστὸν, γάμος πνευματικὸς
καὶ γέννησις πνευματικὴ, οὐκ ἐξ αἱμάτων, οὐκ ἐξ ὠδίνων.”In
Epistulam ad Ephesios, Homily 20.Translation in Schaff,
NPNF1-13, 274.
[27]
“Αἱ γυναῖκες, τοῖς ἰδίοις ἀνδράσιν ὑποτάσσεσθε, ὡς τῷ Κυρίῳ, ὅτι
ὁ ἀνήρ ἐστι κεφαλὴ τῆς γυναικὸς, ὡς καὶ ὁ Χριστὸς κεφαλὴ τῆς
Ἐκκλησίας, καὶ αὐτός ἐστι σωτὴρ τοῦ σώµατος.”In Epistulam ad
Ephesios, Homily 20.
[28]
“‘And the wife see that she reverence her husband- Ἡ δέ γυνή ἵνα
φοβῆται τόν ἄνδρα’: A theological commentary on Ephesians 5:33
by Saint Nektarios, Metropolitan of Pentapolis, 1902,”
republished and translated in English by
OODE, June 22, 2011,
http://www.oodegr.com/english/ekklisia/pateres/Saint_Nektarios_on_woman_respecting_man.htm
[29]
“‘And the wife see that she reverence her husband…”
OODE, June 22, 2011.
[30]
“Ἀλλ' ἄκουσον, ἃ καὶ παρὰ σοῦ ἀπαιτεῖ· πάλιν γὰρ τῷ αὐτῷ
κέχρηται ὑποδείγματι· Οἱ ἄνδρες, ἀγαπᾶτε, φησὶ, τὰς γυναῖκας
ἑαυτῶν, καθὼς καὶ ὁ Χριστὸς ἠγάπησε τὴν Ἐκκλησίαν. Εἶδες μέτρον
ὑπακοῆς; Ἄκουσον καὶ μέτρον ἀγάπης. Βούλει σοι τὴν γυναῖκα
ὑπακούειν, ὡς τῷ Χριστῷ τὴν Ἐκκλησίαν; Προνόει καὶ αὐτὸς αὐτῆς,
ὡς ὁ Χριστὸς τῆς Ἐκκλησίας· κἂν τὴν ψυχὴν ὑπὲρ αὐτῆς δοῦναι δεῖ,
κἂν κατακοπῆναι μυριάκις, κἂν ὁτιοῦν ὑπομεῖναι καὶ παθεῖν, μὴ
παραιτήσῃ· κἂν ταῦτα πάθῃς, οὐδὲν οὐδέπω πεποίηκας, οἷον ὁ
Χριστός.”In Epistulam ad Corinthios, Homily 18.Translation in
Roth and Anderson, St.John
Chrysostom, 46.
[31]
Ὑποθώμεθα οὖν τὸν μὲν ἄνδρα ἐν τάξει κεῖσθαι κεφαλῆς, τὴν δὲ
γυναῖκα ἐν τάξει σώματος.Εἶτα καὶ ἀπὸ λογισμῶν δεικνὺς, Ὅτι ὁ
ἀνὴρ κεφαλή ἐστι τῆς γυναικὸς, φησὶ, καθὼς καὶ ὁ Χριστὸς τῆς
Ἐκκλησίας, καὶ αὐτός ἐστι σωτὴρ τοῦ σώματος.Ἀλλ' ὡς ἡ Ἐκκλησία
ὑποτάσσεται τῷ Χριστῷ, οὕτω καὶ αἱ γυναῖκες τοῖς ἰδίοις ἀνδράσιν
ἐν παντί.Εἶτα, Ὁ ἀνήρ ἐστιν, εἰπὼν, κεφαλὴ τῆς γυναικὸς, ὡς καὶ
ὁ Χριστὸς τῆς Ἐκκλησίας, καὶ αὐτός ἐστι σωτὴρ, ἐπάγει, τοῦ
σώματος· καὶ γὰρ ἡ κεφαλὴ τοῦ σώματος σωτηρία ἐστίν.”In
Epistulam ad Ephesios, Homily 20.Translation in Roth and
Anderson, St. John
Chrysostom, 45.
[32]
Τί δὲ λέγω; καὶ μωρὰ ἦν, καὶ βλάσφημος· ἀλλ' ὅμως τοσούτων ὄντων,
ὡς ὑπὲρ ὡραίας, ὡς ὑπὲρ ἀγαπωμένης, ὡς ὑπὲρ θαυμαστῆς, οὕτως
ἑαυτὸν ἐξέδωκεν ὑπὲρ τῆς ἀμόρφου. Καὶ τοῦτο θαυμάζων ὁ Παῦλος
ἔλεγε· Μόλις γὰρ ὑπὲρ δικαίου τις ἀποθανεῖται· καὶ πάλιν, Εἰ ἔτι
ἁμαρτωλῶν ἡμῶν ὄντων ὁ Χριστὸς ὑπὲρ ἡμῶν ἀπέθανε.Καὶ τοιαύτην
λαβὼν, καλλωπίζει αὐτὴν καὶ λούει, καὶ οὐδὲ τοῦτο παραιτεῖται.”In
Epistulam ad Ephesios, Homily 20.Translation in Scaff,
NPNF1-13, 270.
[33]
“Kἂν τὴν ψυχὴν ὑπὲρ αὐτῆς δοῦναι δεῖ, κἂν κατακοπῆναι μυριάκις,
κἂν ὁτιοῦν ὑπομεῖναι καὶ παθεῖν, μὴ παραιτήσῃ· κἂν ταῦτα πάθῃς,
οὐδὲν οὐδέπω πεποίηκας, οἷον ὁ Χριστός,” In Epistulam ad
Ephesios, Homily 20.Translation in Schaff,
NPNF1-13, 269.
[34]
“σώμα”
የሚለው ‹አካል› ተብሎ
ይተረጎማል፡፡
[35]
“κἂν καταφρονῇ τοῦ σώματος ἡ κεφαλὴ, καὶ αὐτὴ προσαπολεῖται·” In
Epistulam ad Ephesios, Homily 20.
[36] “ἀλλ' ἀντίῤῥοπον τῆς ὑπακοῆς εἰσαγέτω τὴν ἀγάπην.” In Epistulam ad Ephesios, Homily 20.
[37]
የግሪኩ ቃል
‘ἰσοτιµία’
የሚለው ሲሆን ‘ἶσος’
እና
‘τιμή,’ ከተሰኙ ሁለት
ቃላት የተገኘ ነው፡፡ የመጀመሪያው ቃል ትርጉም ‹እኩል› ማለት ሲሆን የሁለተኛው ደግሞ ‹ክብር› የሚል
ነው፡፡
[38]
In Epistulam ad Corinthios, Homily 18.
[39]
“αὐτοῖς τοῖς περὶ τοῦ γάμου λόγοις ἐξαγαγεῖν αὐτοὺς τοῦ γάμου
βουλόμενος. Ὁ γὰρ ἀκούσας ὅτι μετὰ τὸν γάμον οὐκ ἔσται κύριος
ἑαυτοῦ ἀλλ' ἐν τῇ τῆς γυναικὸς κείσεται γνώμῃ ταχέως ἀπαλλαγῆναι
σπουδάσει τῆς πικροτάτης δουλείας, μᾶλλον δὲ μηδὲ τὴν ἀρχὴν τὸν
ζυγὸν ὑπελθεῖν, ἐπειδὴ εἰσελθόντα ἅπαξ δουλεύειν ἀνάγκη λοιπὸν
ἕως ἂν τῇ γυναικὶ τοῦτο δοκῇ.” De Virginitate, Homily 18.
Translation in Miller,
Women, 114.
[40]
Roth and Anderson, St.
John Chrysostom, 86.
[41]
“Πῶς δὲ καὶ γίνονται εἰς σάρκα µίαν; Καθάπερ χρυσοῦ τὸ
καθαρώτατον ἂν ἀφέλῃς καὶ ἑτέρῳ ἀναµίξῃς χρυσῷ, οὕτω δὴ καὶ
ἐνταῦθα, τὸ πιότατον τῆς ἡδονῆς χωνευούσης ἡ γυνὴ δεχοµένη
τρέφει καὶ θάλπει, καὶ τὰ παρ' ἑαυτῆς συνεισενεγκαµένη ἄνδρα
ἀποδίδωσι. Καὶ γέφυρά τίς ἐστι τὸ παιδίον. Ὥστε οἱ τρεῖς σὰρξ
γίνονται µία, τοῦ παιδὸς ἑκατέρωθεν ἑκατέρους συνάπτοντος.”
In
Epistulam
ad
Colossenses,
Homily
12. Translation
in
Schaff,
NPNF1-13,
569.
[42]“…καὶ
λοιπὸν ἡ σὰρξ ὁ πατὴρ καὶ ἡ μήτηρ καὶ ὁ παῖς ἐστιν ἐκ τῆς
ἑκατέρου συνουσίας συγκραθεῖσα· καὶ γὰρ μιγέντων τῶν σπερμάτων,
τίκτεται ὁ παῖς· ὥστε τοὺς τρεῖς εἶναι μίαν σάρκα. Οὕτως οὖν
ἡμεῖς πρὸς τὸν Χριστὸν γινόμεθα μία σὰρξ διὰ μετουσίας· καὶ
πολλῷ μᾶλλον ἡμεῖς, ἢ τὸ παιδίον. Τί δή ποτε; Ὅτι ἐξ ἀρχῆς οὕτω
γέγονε.” In
Epistulam
ad
Ephesios,
Homily
20. Translation
in
Schaff,
NPNF1-13, 272.
[43]
“Μὴ ἀποστερεῖτε ἀλλήλους, εἰ µή τι ἂν ἐκ συµφώνου. Τί δὴ τοῦτό
ἐστι; Μὴ ἐγκρατευέσθω, φησὶν, ἡ γυνὴ, τοῦ ἀνδρὸς ἄκοντος, µήτε ὁ
ἀνὴρ, τῆς γυναικὸς µὴ βουλοµένης. Τί δήποτε; Ὅτι µεγάλα ἐκ τῆς
ἐγκρατείας ταύτης τίκτεται κακά· καὶ γὰρ καὶ µοιχεῖαι καὶ
πορνεῖαι καὶ οἰκιῶν ἀνατροπαὶ πολλάκις ἐντεῦθεν ἐγένοντο. Εἰ γὰρ
ἔχοντες τὰς ἑαυτῶν γυναῖκας, πορνεύουσι, πολλῷ µᾶλλον, ἂν αὐτοὺς
τῆς παραµυθίας ταύτης ἀποστερήσῃς. Καὶ καλῶς εἶπε, Μὴ
ἀποστερεῖτε, ἀποστέρησιν ἐνταῦθα καὶ ὀφειλὴν ἀνωτέρω εἰπὼν, ἵνα
δείξῃ τῆς δεσποτείας τὴν ἐπίτασιν. Τὸ γὰρ ἄκοντος θατέρου
ἐγκρατεύεσθαι θάτερον, ἀποστερεῖν ἐστι·
τὸ δὲ ἑκόντος, οὐκέτι. Οὐδὲ γὰρ, εἰ πείσας µε λάβοις τι
τῶν ἐµῶν, ἀποστερεῖσθαί φηµι. Ὁ γὰρ ἄκοντος καὶ βιαζοµένου λαβὼν,
ἀποστερεῖ· ὅπερ ποιοῦσι πολλαὶ γυναῖκες, µείζονα τῆς δικαιοσύνης
ἁµαρτίαν ἐργαζόµεναι, καὶ τῆς ἀσελγείας τοῦ ἀνδρὸς ὑπεύθυνοι
γινόµεναι ταύτῃ, καὶ διασπῶσαι πάντα. ∆εῖ δὲ πάντων προτιµᾷν τὴν
ὁµόνοιαν, ἐπειδὴ καὶ πάντων τοῦτο κυριώτερον, καὶ εἰ βούλει, καὶ
ἐπὶ τῶν πραγµάτων αὐτὸ ἐξετάσωµεν. Ἔστω γὰρ γυνὴ καὶ ἀνὴρ, καὶ
ἐγκρατευέσθω ἡ γυνὴ µὴ βουλοµένου τοῦ ἀνδρός·
τί οὖν, ἂν ἐκεῖνος ἐντεῦθεν πορνεύῃ, ἢ µὴ πορνεύῃ µὲν,
ἀλγῇ δὲ καὶ θορυβῆται καὶ πυρῶται καὶ µάχηται, καὶ µυρία τῇ
γυναικὶ πράγµατα παρέχῃ; τί τὸ κέρδος τῆς νηστείας καὶ τῆς
ἐγκρατείας, ἀγάπης διεῤῥηγµένης; Οὐδέν. Πόσας γὰρ ἔνθεν
λοιδορίας, πόσα πράγµατα, πόσον ἀνάγκη γίνεσθαι πόλεµον.”
In
Epistulam
ad
Corinthios,
Homily
19. Translation
in
Schaff,
NPNF1-12,
186-187.
[44]
“Ὅτι πολλὴ ἡ τοῦ γάμου δουλεία καὶ ἀπαραίτητος. Τί οὖν ἐὰν μὲν ὁ
ἀνὴρ ἐπιεικὴς ᾖ, ἡ δὲ γυνὴ μοχθηρά, λοίδορος, λάλος, πολυτελής,
τὸ κοινὸν τοῦτο πασῶν αὐτῶν νόσημα, ἑτέρων πλειόνων γέμουσα
κακῶν, πῶς οἴσει τὴν καθημερινὴν ταύτην ἀηδίαν ἐκεῖνος ὁ
δείλαιος, τὸν τῦφον. τὴν ἀναισχυντίαν; Τί δαί, ἂν τοὐναντίον
αὐτὴ μὲν ᾖ κοσμία καὶ ἥσυχος, ἐκεῖνος δὲ θρασύς, ὑπεροπτικός,
ὀργίλος, πολὺν μὲν ἀπὸ τῶν χρημάτων, πολὺν δὲ ἀπὸ τῆς δυναστείας
ὄγκον περιβεβλημένος, καὶ τὴν ἐλευθέραν ὡς δούλην ἔχει καὶ τῶν
θεραπαινίδων μηδὲν ἄμεινον πρὸς αὐτὴν διάκειται, πῶς οἴσει τὴν
τοσαύτην ἀνάγκην καὶ βίαν; Τί δαί, ἂν συνεχῶς αὐτὴν ἀποστρέφηται
καὶ διὰ παντὸς μένῃ τοῦτο ποιῶν; Καρτέρει, φησίν, πᾶσαν ταύτην
τὴν δουλείαν· ὅταν γὰρ ἀποθάνῃ, τότε ἐλευθέρα ἔσῃ μόνον, ζῶντος
δὲ δυοῖν θάτερον ἀνάγκη, ἢ παιδαγωγεῖν αὐτὸν μετὰ πολλῆς τῆς
σπουδῆς καὶ βελτίω ποιεῖν ἤ, εἰ τοῦτο ἀδύνατον, φέρειν γενναίως
τὸν ἀκήρυκτον πόλεμον καὶ τὴν ἄσπονδον μάχην.” DeVirginitate,
Paragraph 40.
[45]
“Τί οὖν ἐὰν μὲν ὁ ἀνὴρ ἐπιεικὴς ᾖ, ἡ δὲ γυνὴ μοχθηρά, λοίδορος,
λάλος, πολυτελής…; Τί δαί, ἂν τοὐναντίον αὐτὴ μὲν ᾖ κοσμία καὶ
ἥσυχος, ἐκεῖνος δὲ θρασύς, ὑπεροπτικός, ὀργίλος, πολὺν μὲν ἀπὸ
τῶν χρημάτων, πολὺν δὲ ἀπὸ τῆς δυναστείας ὄγκον περιβεβλημένος…”
De Virginitate, Paragraph 40.
[46]
በኦርቶዶክስ
ትውፊት
ዶግማና
የነገረ
መለኮት
ጉዳይያልሆኑ
የአባቶች
ትምህርቶች
እንደምክር
ነው
የሚወሰዱት፡፡
ስለዚህ
ባሏ
ክፉ
የሆነባት
አንዲት
ሴት
ምን
ታድርግ
ለሚለው
አንድ
ወጥ
የሆነ
አቋም
ላይኖር
ይችላል፡፡
ይሄ
በሴቷ
የቤተሰብ
አስተዳደር
መርህና
የምርጫ
ውሳኔ
ላይ
የሚወሰን
ነው፡፡
[47]
“Μὴ λεγέτω ταῦτα γυνὴ, καὶ τὰ τούτοις ὅμοια· σῶμα γάρ ἐστιν, οὐχ
ἵνα διατάττῃ τῇ κεφαλῇ, ἀλλ' ἵνα πείθηται καὶ ὑπακούῃ. Πῶς οὖν
οἴσει, φησὶ, τὴν πενίαν; πόθεν εὑρήσει παραμυθίαν; Ἐκλεγέσθω
παρ' ἑαυτῇ τὰς πενεστέρας, ἀναλογιζέσθω πόσαι πάλιν εὐγενεῖς καὶ
ἐξ εὐγενῶν κόραι οὐ μόνον ἐξ ἀνδρῶν οὐδὲν προσέλαβον, ἀλλὰ καὶ
προσέδωκαν, καὶ τὰ αὐτῶν ἅπαντα ἀνάλωσαν· ἐννοείτω τοὺς ἐκ
τοιούτων πλούτων κινδύνους, καὶ τὸν ἀπράγμονα ἀσπάσεται βίον.Καὶ
ὅλως εἰ φιλοστόργως πρὸς τὸν ἄνδρα διακέοιτο, οὐδὲν τοιοῦτον
ἐρεῖ, ἀλλ' αἱρήσεται πλησίον αὐτῆς ἔχειν αὐτὸν μηδὲν πορίζοντα,
ἢ μυρία τάλαντα χρυσοῦ μετὰ μερίμνης καὶ φροντίδος τῆς ἐκ τῶν
ἀποδημιῶν ταῖς γυναιξὶν ἐγγινομένης ἀεί.”In Epistulam ad
Ephesios, Homily 20. Translation in Schaff,
NPNF1-13, 278-279.
[48]
“οὐ φόβῳ καὶ ἀπειλαῖς δεῖ καταδεσμεῖν, ἀλλ' ἀγάπῃ καὶ διαθέσει.”
In Epistulam ad Ephesios, Homily 20.Transaltion in Schaff,
NPNF1-13, 270.
[49]
“Ἀλλὰ μηδὲ ὁ ἀνὴρ ταῦτα ἀκούων ὡς ἀρχὴν ἔχων, ἐπὶ ὕβρεις
τρεπέσθω καὶ πληγὰς, ἀλλὰ παραινείτω, νουθετείτω, ὡς ἀτελεστέραν
λογισμοῖς ἀναπειθέτω, χεῖρας μηδέποτε ἐντεινέτω· πόῤῥω ἐλευθέρας
ψυχῆς ταῦτα· ἀλλὰ μηδὲ ὕβρεις, μηδὲ ὀνείδη, μηδὲ λοιδορίας· ἀλλ'
ὡς ἀνοητότερον διακειμένην ῥυθμιζέτω.”In Epistulam ad Ephesios,
Homily 20.
[50]
“Οἰκέτην μὲν γὰρ φόβῳ τις ἂν καταδῆσαι δυνήσεται, μᾶλλον δὲ οὐδὲ
ἐκεῖνον· ταχέως γὰρ ἀποπηδήσας οἰχήσεται· τὴν δὲ
τοῦ βίου
κοινωνὸν,
τὴν
παίδων
μητέρα,
τὴν
πάσης
εὐφροσύνης
ὑπόθεσιν,
οὐ φόβῳ
καὶ
ἀπειλαῖς
δεῖ
καταδεσμεῖν,
ἀλλ'
ἀγάπῃ καὶ
διαθέσει.
Ποία γὰρ
συζυγία,
ὅταν
ἡ
γυνὴ
τὸν ἄνδρα
τρέμῃ;
ποίας
δὲ
αὐτὸς ὁ
ἀνὴρ
ἀπολαύσεται
ἡδονῆς,
ὡς
δούλῃ
συνοικῶν
τῇ γυναικὶ,
καὶ
οὐχ
ὡς
ἐλευθέρᾳ;
Κἂν πάθῃς
τι
ὑπὲρ
αὐτῆς,
μὴ
ὀνειδίσῃς·
οὐδὲ
γὰρ ὁ
Χριστὸς
τοῦτο ἐποίησε.”
In Epistulam ad Ephesios, Homily 20.
[51]
“Ἀλλ' ὅταν ἀκούῃς φόβον, ἐλευθέρᾳ προσήκοντα φόβον ἀπαίτει, μὴ
καθὼς παρὰ δούλης· σῶμα γάρ ἐστι σόν· ἂν γὰρ τοῦτο ποιήσῃς,
σαυτὸν καθυβρίζεις, τὸ σῶμα ἀτιμάζων τὸ σόν.”In Epistulam ad
Ephesios, Homily 20.Translation from Schaff,
NPNF1-13, 275.
[52]
“Οὐδεὶς γάρ ποτε τὴν ἑαυτοῦ σάρκα ἐμίσησεν.”In Epistulam ad
Ephesios, Homily 20.
[53]
“Μὴ δι' ἐκείνην τοίνυν τοσοῦτον, ὅσον διὰ τὸν Χριστὸν αὐτὴν
ἀγαπᾷν.”In Epistulam ad Ephesios, Homily 20.Translation in
Schaff, NPNF1-13, 277.
[54]
“Τί οὖν, ἂν μὴ φοβῆται, φησὶν, ἡ γυνή; Σὺ ἀγάπα, τὸ σαυτοῦ
πλήρου.Καὶ γὰρ ἂν τὰ παρὰ τῶν ἄλλων μὴ ἕπηται, τὰ παρ' ἡμῶν
ἕπεσθαι δεῖ. Οἷόν τι λέγω· Ὑποτασσόμενοι, φησὶν, ἀλλήλοις ἐν
φόβῳ Χριστοῦ. Τί οὖν, ἂν ὁ ἕτερος μὴ ὑποτάσσηται; Σὺ πείθου τῷ
νόμῳ τοῦ Θεοῦ. Οὕτω δὴ καὶ ἐνταῦθα· ἡ γοῦν γυνὴ κἂν μὴ ἀγαπᾶται,
ὅμως φοβείσθω, ἵνα μηδὲν ᾖ παρ' αὐτῇ γεγονός· ὅ τε ἀνὴρ, ἂν μὴ
φοβῆται ἡ γυνὴ, ὅμως ἀγαπάτω, ἵνα μηδὲν αὐτὸς ὑστερῇ· ἕκαστος
γὰρ τὸ ἴδιον ἀπέλαβεν.” In Epistulam ad Ephesios, Homily
20.Translation in Schaff,
NPNF1-13, 274.
[55]
“Τί οὖν ἐστιν, ὃ τοῖς γεγαμηκόσι παρήγγειλεν ὁ Κύριος, Γυναῖκα
ἀπὸ ἀνδρὸς μὴ χωρισθῆναι; ἐὰν δὲ καὶ χωρισθῇ, μενέτω ἄγαμος, ἢ
τῷ ἀνδρὶ καταλλαγήτω· καὶ ἄνδρα γυναῖκα μὴ ἀφιέναι; Ἐπειδὴ γὰρ
καὶ δι' ἐγκράτειαν καὶ δι' ἄλλας προφάσεις καὶ μικροψυχίας
γίνεσθαι διαιρέσεις συνέβαινε, βέλτιον μὲν μηδὲ γενέσθαι τὴν
ἀρχὴν, φησίν· εἰ δὲ ἄρα καὶ γένοιτο, μενέτω ἡ γυνὴ μετὰ τοῦ
ἀνδρὸς, εἰ καὶ μὴ τῇ μίξει, ἀλλὰ τῷ μηδένα ἕτερον παρεισαγαγεῖν
ἄνδρα.” In Epistulam i ad Corinthios, Homily 19.Translation in
Schaff, NPNF1-12, 188.
[56]
ጥንዶቹ
ክርስቶስንና
ቤተክርስቲያንን
ወደ
መምሰል
ጸባያቸውን
ከለወጡ
ዕርቅ
ሊመጣ
እንደሚችል
የታወቀ
ነው፡፡
በኦርቶዶክሳዊ
መንገድ
የሚሆን
ዕርቅ
ደግሞ
ኃጢአት
የሆነውን
ፍቺን
የሚያርቅ
ብቻ
ሳይሆን
የላቀ
ትሕትናን (ችግርንና
ስሕተትን
አምኖ
መቀበልን)
፣
መልካምነትንና
ተግባቦትን
በጥንዶቹ
መሀል
የሚያመጣና
አንዳቸው
ለአንዳቸው
የተሻለ
እንክብካቤን
እንዲችሩ
የሚያደርግ
ውሕደትን
የሚያመጣ
ነው፡፡
ምዕራፍ 4 | ወደ ይዘቶች ተመለስ | ምዕራፍ 6 |
Δεν υπάρχουν σχόλια:
Δημοσίευση σχολίου