Πέμπτη 30 Αυγούστου 2018

ኢትዮጵያዊው ሙሴ፣ጥቁሩ ቅዱስ እና መምህሩ (እና ሌሎችም የኦርቶዶክስ ቤተ - ክርስቲያን ቅዱሳን ኢትዮጵያውያን)


እኛ የግሪክ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ነን፡፡ ኦርቶዶክስ ስለሆንን አገራችንን እንወዳለን፣ ህዝባችንንና መላው የአለማችንን ህዝብ አፍሪካዊ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን ጨምሮ፡፡

ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ሙሴ   


ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ሙሴ በመጀመሪያ የወንበዴዎች መሪ፣ ገዳይ እና በጥንታዊቷ አፍሪካም ሌባ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ እሱ የለውጥ አርአያ ሆነ፡፡ ከአፍሪካ ቅዱሳኖች መካከል የሱ የሚያስደምም ነው፡፡ ከባርነት ያመለጠው ሙሴ የ 75 ሌቦች አለቃ ነበር፡፡
ከዱርዬዎቹ ጋር ሙሉ ከተማዋን ያሸበረ ግዙፍና ሃይለኛ ሰው ነበር፡፡ ሙሴ የተለወጠው እሱና ቡድኑ ለስርቆት ቤተ ከመቅደስን ያጠቁ ጊዜ ነበር፡፡ እዛ አንድ ስነ-ስርኣት ያለው ሰው አገኘውና በጣም ተነካ፡፡ በቅጽበትም ስለሰራቸው ሀጥያቶች ጸጸት ተሰማው፣ ንስሃም ገባ እናም እዛው ቤተ መቅደሱ ውስጥ እንዲቆይ ለመናቸው፡፡ ሙሴ ለአመታት በድሮ ህይወቱ ተሰቃየ፤ እናም ወደነበረው መንገዱም ለመመለስ ጓጓ፡፡ አንድ ቀን ሀጥያቶቹን ለ ቅዱስ ማካሪየስ በመናዘዝ ላይ ሳለ አንድ መልአክ የሀጥያቶቹን ዝርዝር ይዞ በፊቱ ቀረበ፡፡ ሲናዘዝም መልአኩ ሀጥያቶቹን አንድ በአንድ መሰረዝ ጀመረ፡፡ ብዙ ሲናዝዝ ብዙ ይሰርዝለታል፡፡ ቅዱስ ማካሪየስንና ቅዱስ ኢሲዶርን ክተዋወቀ በኋላ የቀድሞ መንገዱን እርግፍ አድርጎ ትቶ መነኩሴ ሆነ፡፡ ከዛም ቅዱስ ሙሴ ለቅስና ተሸመ፤ ይህ ለበረሃ አባቶች አንድ አንዴ የሚገኝ ክብር ነው፤ ሄዶም 75 መነኩሳን ያሉበት ቤተ መቅደስ አገኘ፣ ልክ እንደ ቀድሞው ሌቦቹ ቁጥር፡፡ በጥበቡ፣ በትህትናው፣ በፍቅሩ እናም ማንም ላይ ባለምፍረዱ ይታወቅ ነበር፡፡ አንድ ጊዜ አንድ ወንድም በተመሳሳይ ሃጥያት ከተያዘ በኋላ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዩ ቅዱስ ሙሴ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ መጥቶ ፍርድ እንዲፈርድ ጠየቀው፡፡ እሱም ሳይፈልግ በጀርባው አሸዋ የተሞላበት ቀዳዳ ቦርሳ ይዞ ሄደ፡፡ ከቦታው ሲደርስ የተያዘው ወንድም ለምን እንደዚህ አይነት ነገር እንደተሸከመ ጠየቀው፡፡ እርሱም ቀለል አድርጎ “ይሄ አሸዋ የሌላ ሰው ሀጥያት ለመፍረድ ስሄድ ከኋላዬ እየቀረ የመጣው ሃጥያቶቼ ነውˮ አለው፡፡ ይህንን መልስ ሰምተው ሀጥያተኞቹ ወንድሞች የበደላቸውን ይቅር በማለት የሌሎች ወንድሞች ሀጥያት ላይ ከማተኮር ይልቅ የራሳቸው ድነት ላይ ማተኮር ጀመሩ፡፡
 405 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ቤተ መቅደሱ በዱርዬዎች ተጠቅቶ 75 አመቱ ቅዱስ ሙሴ  አረፈ፡፡ በነሀሴ 22 ተዘክሮ ይውላል፡፡ የወንድማማችነታችንም ጠባቂ ነበር፡፡



ሌሎች ኢትዮጵያውያን ቅዱሳን በምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስትያን

ሰማእት ጃን ዳራዳ ( ስምዖን ባቾስ) ጃንደረባው የንግስት ካንዴስ ኢትዮጵያዊ (የሚዘከርበት ቀን ነሀሴ 22)



           
ቅዱሰ ፊሊጶስ ኢትዮጵያዊው ዲያቆን እና ደረባ


ጃንደረባው ኢትዮጵያዊ በመጽሃፍ ቅዱስ በአዲሰ ኪዳን ውስጥ ይገኛል፡፡ ወደ ክርስትና እንዴት እንደተለወጠ  በ ሃዋርያት ስራ ምዕራፍ 8 ላይ ታሪኩ ተገልጿል፡፡

የመጽሃፍ ቅዱሰ ትንተና

ወንጌላዊው ፊሊጶስ ከእየሩሳሌም እስከ ጋዛ ባለው መንገድ እንዲወርድ በመልአክ ተነገረው፡፡ ተነስቶም ሄደ፡፡ እነሆም ህንደኬ የተበለች የኢትዮጵያ ንግስት አዛዥና ጃንደረባ የነበረ በገንዘብዋም የሰለጠነ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር፡፡ (የሃዋርያት ስራ 8፡27) ሲመለስም በሰረገላ ተቀመምጦ የነብዩን የኢሳያስን መጽሓፍ ያነብ ነበር፡፡ መንፈስም ፊሊጶስን ወደዚህ ሰረገላ ቅረብና ተገናኝ አለው፡፡ ፊሊጶስም ሮጦ የነብዩን መጽሓፍ ሲያነብ ሰማና፣ በውኑ የምታነበውን ታስተውለዋለህ? አለው፡፡ እርሱም የሚመራኝ ሳይኖር ይህ እንዴት ይቻለኛል? አለው፡፡ ወጥቶም ከእርሱ ጋረ ይቀመጥ ዘንድ ፊሊጶስን ለመነው፡፡ ፊሊጶስም አፉን ከፈተ ከዚህም መጽሓፍ ጀምሮ ስነኢየሱስ ወንጌል ሰበከለት፡፡ በመንገድ ሄዱ ወደውሃ ደረሱ፤ ጃንደረባውም እነሆ ውሃ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምንድን ነው? አለው፡፡ ፊሊጶስም በፍጹም ለልብ ብታምን ተፈቅዷል አለው፡፡                                                                                            በንጉስ ጄምስ  እና በካቶሊክ ኢትዮጵያዊው የሚለው “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሄር ልጅ እንደሆነ አምናለሁˮ አለ (ቁጥር 37)  ነገር ግን በአዳዲስ ህትመቶች ላይ ይሄ የለም፡፡ ቢሆንም ግን የኢትዮጵያው የሓዋርያት ስራ በጣም በጥሩ ሁኔታ የተተረጎም ነው፡፡
ከውሃውም ከወጡ በኋላ የጌታ መንፈስ ፊሊጶስን ነጠቀው፡፡ ጃንደረባውንም ሁለተኛ አላየውም፡፡ ደስ ብሎት መንገዱን ይሄድ ነበረና፡፡ (ቁጥር 39)

ክርሰቲያናዊ ልማዶች 

ሊዮናዊው ቅዱሰ ኢራኒየስ በመጽሃፋቸው 'አድቨርሰስ ሄረስስ` (ጸረ መንፈሳዊ ትምህርቶች) 3፡12፡8 (180 AD) ስለ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ነው የተጻፈው፡፡ ይህ ጃንደረባው ስምኦን ባቾስ የተባለው ሰው ወደ ኢትዮጵያ ሀይማኖቶችም ያመነውን እንዲሰብክ፣ በነቢያት እንደተሰበከው አንድ አምላክ ብቻ እንዳለ፣ ነገር ግን የእግዚአብሄር ልጅ ስጋ ለብሶ እንደመጣ፣ ለእርድ እንደተዘጋጀ በግ እንደመጣ እናም ነብያትም እንዲህ ብለው እንደተናገሩለት ˮበኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልማዶች ባቾስ ተብሎ እንደሚጠራ፣ በምስራቃዊው ኦርቶዶክስ ልማዶች ደግሞ ስምኦን ተብሎ ይተሰየመው ኢትዮጵያዊው ቤተ እስራኤላዊ፣ በሃዋርያት ስራ ላይም 13፡1 እንደሚጠራው እንዲናገር ተልኮ ነበር፡፡
 
ግምገማና ትርጓሜ


ይህ ኢትዮጵያዊ ጃንደባና በንግስት ካንዴስ ፍርድቤት ውስጥም የገንዘብ ሹም  ነው (የሃዋርያት ስራ 827) ተከታይ እንዲሆን ታስቦ ነበር ቢሆንም ግን ፖል ሙሞ ቄሳው ፈሪሃ እግዚአብሄር ያለው ሰው እንደሆነ ተከራክረውለታል፡፡ ስኮት ሻፍ ባከረቡት ሀሳብ መሰረት ˮየዚህ ታሪክ ዋና አላማ ወንጌልን እስከ አለም ፍጻሜ ድረስ ማድረስ ነው እንደሆነ እንጂ እምነት የለሽ ተልእኮን ማቋቋም እንዳልሆነ እናም ሉቃስ የኢትዮጵያውያንን እምነት የለሽነትን አያስቀምጥም፡፡ ነገር ግን ጃንደረባው ምናልባት እምነት የለሽ ሆኖ መገለጹ አንባቢው በታሪኩ በሁኔታው ሚስጥራዊነት እንዲሳብ ያደርገዋን፡፡ ጃንደረባው ከኑቢያ ወይም ከሱዳን ይሆናል፡፡ ዴቪድ ቲዩስደይ አዳሞ እንዳለው ከሆነ አይቲዮፕስ የተባለው ቃል በቀላሉ ሲተረጎም አፍሪካ ማለት ነው፡፡ በአጠቃላይ ዘጋቢዎቸሀ እንደሚሉት ከሆነ ጃደረባና የፍርድቤት ሹም የሚለው ስያሜ አንድ ላይ የሚያመላክተው 5ኛው የሙሴ መጽሀፍ 231 እንደሚከለክለው ከቤት መቅደሱ እንደሚወገድ ነው፡፡ አንዳንድ ምሁራን ጃንደረባዎች ከአይሁድ አምልኮ ይወገዙ እንደነበር እናም በአዲሰ ኪዳንም እነዚህን ወንዶች ከአነስተኛ የጾታ ወገን እንደመደቧቸው ያመለክታሉ፡፡ ጆን መክኔይል በአዲሰ ኪዳን በማቴዎስ ወንጌል 1912 ይህ ጃነደረባ የመጀመሪያው የተጠመቀ ግብረ-ሰዶማዊ ክርስትያን ነበር፤ ብሎ ሲጠቅስ ጃክ ሮጀርስ ደግሞ ˮእውነታው እንደሚጠራው ከሆነ የመጀመሪያው ወደ ክርስቲያን የተቀየረው ጃንደረባ የመጣው ከአናሳና ከተለያየ ዘር፣ ጎሳ እና ዜግነት መሆኑ ክርስቲያኖች የሚያጠቃልሉ እና ጥሩ ተቀባይ መሆናቸውን ያሳያል ብሎ ጻፈ፡፡

             

ምስሉ ከ ሜኖሎጂያን ባስልእል 2፤ የፊሊጶስ እና ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ምስል


ሌሎች ምሁራን ስለ ጃንደረባው ዘርም አንስተዋለ፡፡ አንዳነድ እንደ ፍሬንክ ኤም ስኖውደን ጁኒየር በአጋንኖ ስለ ቀደምት ክርስትያናዊ ማህበረሰቦች ዘርን ባላማከለ ሁኔታ አባላትን ይቀበሉ ነበር፡፡ ኢትዮጵያውያን በድሮ ዘመን በቆዳ ቀለም ይመዝኑ/ይለዩ ነበር፡፡ ሌሎችም እንደ ክላሪሰ ማረቲነ ያሉ እንደጻፉት ˮየተሰጠው ዘገባ ስለ ሀይማኖቱ እንጂ ስለ አጥባቂቆቹ አይደለም፡፡ˮ ጋይ ኤል ባይረን ሲጨምር ˮኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ የተጠቀመው ሉቃስ ሲሆን የጠቀሰውም ድነት ወደ ኢትዮጵያውያንና ጥቁሮች ሊሰፋፋ እንደሚችል ለማመልከት ነው፡፡
ቤሬት የጃንደረባውን ታሪክ ሌላው ወደ ክርስቲያን ተቀያሪ ከሆነው የጦር አዛዡ ቀርኔሊዮስ ጋር ያነጻጽረዋል፡፡ ጃንደረባው ጉዞውን ሲቀጥልና ከትረካው ቢወጣም ቀርኔሊዮስና ከጁዳ ቤተክርስቲያን የሆኑት ተከታዮቹ ከፊሊጶስ ይልቅ ጴጥሮስ ላይ ማተኮርን መረጡ፡፡ ሮበርት ኦቶሌ ፊሊጶስ እንደ ኢየሱስ ከንግግር በኋላ ከእይታ መጥፋቱን ይቃወማል፡፡

ቅዱስ ፉልቪያን ማቲው የኢትዮጵያ ንጉስ


ቅዱሱ ሀዋርያ የክርስቶስን ወንጌል ወደ ሲሪያ፣ ሜዲያ፣ ፐርዢያ፣ ፓረቲያ በመጨረሻም ስብከቱን ኢትዮጵያ ውስጥ ሰማዕት ሆኖ ጨረሰ፡፡ ቅዱስ ሀዋርያ ማቴዎስ የተወሰኑ ጣዖት አምላኪዎችን ወደ ክርስቶስ እምነት ቀይሯቸዋል፡፡ ቤተክርስቲያን አጊኝቶ ሚርሜና ከተማ ውስጥ ቤተ-መቅደስ ሰራና አጋሩን ፕላቶን ቄስ አድርጎ ሾመው፡፡
ቅዱሱ ሃዋርያ ከኢትዮጵያውያን ጋር እንዲያወራ እግዚብሄርን አጥብቆ ሲለምነው፣ ራሱ ጌታ በወጣት ተመስሎ እሱ ጋር መጣ፡፡ ዱላም ሰጠው፤ በቤተ-ክርስቲያኑ ደጃፍም እንዲተክለው አዘዘው፡፡ ጌታመ ዛፍ ክሱ ያድጋለ፣ ፍሬም ያፈራል ከስሮቹም ውሃ ይፈልቃል፡፡ ኢትዮጵያዊያኑ በምንጩ ሲታጠቡና  ፍሬውንም ሲበሉ የእብደት መንገዳቸውን ትተው ጨዋና ጥሩ ሆኑ፡፡
ቅዱስ ሀዋርያ ዱላውን ወደ ቤት ክርስቲያኑ ይዞ እየመጣ እያለ መንገድ ላይ ከመሬቱ ገዢ(በእርኩሰ መናፍስት ተይዞ ነበር) ልጅና ሚስት ጋር ተገጣጠመ፡፡ በክርስቶስ ስም ቅዱሰ ሃዋርው አዳናቸው፡፡ይህ ታአምር በብዙ ቁጥር የሚጠጉ አረመኔዎችን ወደ ጌታ ለወጣቸው፡፡ ነገር ግን ገዢው ሰዎቹ ክርስቲያን እንዲሆኑና ጣኦት ማምለካቸውን እንዲያቆሙ አልፈለገም፡፡ ሃዋርያውን በጥንቆላ ወንጅሎ እንዲገደል ትእዛዝ አስተላለፈ፡፡
የቅዱስ ማቴዎስን ጭንቅላት ወደታች አቅዝቀው እንጨት ደረቡበትና አቃጠሉት፡፡ እሳቱ ሲነበለነል ሁሉም ሰው እሳቱ ክዱስ ማቴዎስን እንዳልጎዳው አየ፡፡ ከዛም ፉልቪያን ተጨማሪ እንጨት እንዲጨመር አዘዘ፤ በድፍረትም ተሞለቶ 12 ጣኦቶች በእሳቱ ዙሪያ እንዲደረደሩ አዘዘ፡፡ ግን እሳቱ ጣኦቶቹን አቀለጠ፤ ወደ ፉለቪያንም ቦግ አለ፡፡ የደነገጡት ኢትዮጵያውያንም ወደ ቅዱሱ በመዞር ምህረትን ለመኑ እናም በሰማእቱ ጸሎት እሳቱ ጠፋ፡፡ የቅዱስ ሀዋርያውም ሰውነት ምንም ጉዳት ሳይደርስበት ወደ ጌታ ሄደ፡፡
ገዢው ፉለቪያን ስለተግባሩ በጣም ተጸጸተ፤ አሁንም ግን ጥርጣሬ ነበረው፡፡ በራሱ ትእዛዝም የቅዱስ ማቴዎስንም አስከሬኑን በብረት ሬሳ ሳጥን ውስጥ አስገብተው ወደባህር ወረወሩት፡፡ ይህን ሲያደርግ ፉቪያን ˮየማቴዎስ አምላክ የሀዋርያውን ሰውነት ምንም ሳይቀየር በእሳቱ እንዳቆየው በውሃም ካቆየው ይህ አንዱን እውነተኛ አምላክ ለማምለክ ተገቢ ምክንያት ይሆናልˮ ብሎ ተናገረ፡፡
ያን ምሽትም ሀዋርያው ማቴዎስም በቅስ ፕላቶን ህልም ውስጥ ተገለጠ እናም ሬሳውን ለመፈለግ ከካህናት ጋር ወደባህሩ ዳርቻ እንዲሄዱ አዘዘው፡፡ ጻድቁ ፉልቪያን እና የክብር ተከታዮቹ ከቅሱ ጋረ ወደ ባህር ዳርቻው ሄዱ፡፡ የሬሳ ሳጥኑም በማእበል ተሸክሞ ወደ ሀዋርያው ወደሰራው ቤተ-ክርስቲያን ተወሰደ፡፡ ከዛም ፉልቪያን ቅዱስ ሃዋርያ ማቴዎስን ይቅርታ ለምኖ ቄስ ፕላቶነ አጠመቁት፤ የአምላክ ትእዛዝንም በመታዘዝ ማቴዎስ የሚል ስምም ሰጡት፡፡
በቅርቡም ግዛቱን ትቶ ቀሲስ ሆነ፡፡ በቄስ ፕላቶን ሞት ጊዜም ሃዋርያው ማቴዎስ ተገልጠው ወደኢትዮጵያ ቤተ-ክርስቲያን እንዲሄድ አሳሰቡት፡፡ ቄስ ከሆኑ በኋላ ቅዱስ ፉለቪያን ማቴዎስ የመንግስተ ሰማያትን በጎ ስራ በመቀጠል የእግዚአብሄርን ቃል በመስበክ ታተረ፡፡

ኢትዮጵያዊው ባሪያ ሰማዕቱ ቅዱስ ክሪሰቶዶሎስ 

ከቅድስት ከርካይራ ልእልቷና ድንግሏ ሰማእት

ቅድስት ከረኪራ

ቅድስት ከርካራ አረማዊ ከሆነው የከርኪራ ንጉስ ከርኪሎኖስ ልጅ ነበረች፡፡ ቅን ስለነበረች የእሷ እውነተኛውን እምነት ማወቅ ከዛም በቅዱስ ጥምቅት የቤተ-ክርስቲያን አባል መሆኗ ለእግዚአብሄር በጣም አስደሳች ነበር፡፡ በህይወቷም ሀዋርያ ጄሰን እና ሶሲፓተርን አወቀች፡፡ እነዚህ ሀዋርያት ከርኪራ ውስጥ ወንጌልን ይሰብኩ ነበር፡፡ በአረማዊው ንጉስ ከርኬሊዮንም ታሰረው በጠይቀው፣ በጣም ተሰቃይተው  ወደ እስር ቤት ተላኩ፡፡ ቅድስት ከረኪራ በቅዱሳኑ ጉብዝናቸው፣ ድፍረትና ጀግንነት፣ ትእግስጸኛነታቸውና ፊታቸው ላይ በሚታየው የመልአክ ብርሃን አድናቆት አደረባት፡፡
ሀዋርያቱ እስር ቤት እንኳን ቢሆኑም ወንጌል መስበካቸው ግን አላቋረጡም፡፡ እንዲህም እያደረጉ 7 ወንበዴዎች፣ የእስር ቤቱ ጠባቂ አንተኒ እና የከርኪሊኖስን ልጅ ከርኪራን ወደ እምነታቸው ሳቧቸው፡፡ ከርኪራ ክርስቲያን መሆኗ ህዝቡ ላይ ታላቅ አግርሞት አግኝቶ ነበር፡፡ ስለዚህም አማኞቹ ቁጥራቸው ጨመረ፡፡ ከርኪሊኖሰ ስለዚ ባወቀ ጊዜ ልጁን አስጠርቶ ለማግባባት ሞከረ፡፡ የማይቻል ሆነበት፡፡ በታላቅ ቁጣም እንድትታሰር አዘዘ፡፡ ወደ እስር ፤ቤቷም ኢትዮጵያዊ ልኮ ሀሳቧ እንዲበከልም ጣረ፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያዊው እስር ቤቱን በር በቀረበ ጊዜ በአውሬ ተጠቅቶ ክፉኛ ተጎዳ፡፡ በሷ ጸሎትም ቅዱሳኑ አዳኑት፤ እንዲመሰክርም ተደረገ፡፡ በውጤቱም  የእውነተኛ እምነቱ መስካሪና የክርስቶስ ሰማእት ሆነ፡፡
ቅድስት ከርኪራ ጣእት አምላኪው አባቷ በጣም ተሰቃየች፡፡ በድጋሚም የክርስቶስን ቃል አለጋገጠች ˮጠላቶቻቹ በቤታች ውስጥ የሚኖሩት ናቸውˮ እስከ ሞቷም ድረስ ጸንታ ቆየች፡፡ በቀስቶችም ወግተው ገደሏት፡፡ ከህያው እግዚአብሄር ዘንድም ነፍሷን አሳልፋ ሰጠች፡፡

ኢትዮጵያዊው ንጉስ  ቅዱስ ኤለስባን


             
ከታች ቅዱሳን ሶፊያ፤ ፉለቫነስ-ማቴዎስ፤ ነንተኒ ኤለስባን፣ ኢትዮጵያዊው ሙሴ
ሲፐሪያን፣ ጃን ዳራ፣ ሞውሪስ፣ አታናሲየስ እና ግብጻዊቷ ማርያም 
 
6ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ከህጻንነቱ ጀምሮ በካቶሊክ እምነት ባደገው በጥቁሩ ንጉስ ቅዱስ ካሌብ ወይም ኤለስባን (ባህታዊ ከሆነ በኋላ) ትመራ ነበር፡፡ (ካቶሊክ = ኦርቶዶክስ ) ንጉስ ኤለስባን አገሩን በጥበብ ይመራት ስለነበር በህዝቦቹ  አድናቆት ነበረው፡፡
በዛን ጊዜ ኢትዮጵያ በጀስቲኒያን 1 ስር በሚተዳደረው  የምስራቅ ሮማን ግዛት ክፍል ነበረች፡፡ ቀይ ባህርን አቋርጦ አረቢያ የካቶሊክ እምነቱን ክዶ ጁዲሂዝምን የተከተለው ንጉሰ ዱናን ስር ነበረች፡፡ ጨቋኝ መሪ ነበር፡፡ ጳጳሱንና ካህናቱን ገድሎ፤ አብያተ ክርስቲያናትን አውድሞ ወይም ወደ አይሁድ ቤተ-መቅደስነት ይቀይራቸዋል፡፡ ቅዱስ ግሬጌንቲየስ፤ የታፋስ ጳጳስ ከደብራቸው ተባረው ነበር፡፡ ቅዱስ አሬታስ፣ የናግራን አስተዳዳሪን የካቶሊክ መሪ ከሚሰታቸው፤ ልጆቻቸው እና 340 ህዝቦቻቸው ጋር ተሰይፈዋል፡፡ 4000 ኦርቶዶክሶች ከብዙ ጭካኔ በኋላ ካለምንም ፍርድ ተገድለዋል፡፡

 
ቅዱስ ኤለስባን ኦርቶዶክስ
           
ባህታዊ ሆኖ ተራሮች ላይ ወደሚገኘው ገዳም ውስጥ ገባ፡፡ እዛም እንደ አንድ ተራ ሀይማኖተኛ በመጸለይ፣ በመታዘዝና በመስራት ኖረ፡፡
በቅድስና ዝና .. ጥቅምት 27 532 አረፈ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ብቸኛ ባህታዊ ሆኖ መስቀል ይዞ እግሩ ላይም ዘውዱን አስቀምጦ ነው ፎቶ ያለው፡፡

የነብዩ ፕሊኒዮ አስተያት
 
እንደማስበው የቅዱስ ኤሌስባ ህይወት የተለየ ውበት ያለውና በተለይ በምስራቅ ካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያንን የህይወት ትርእይትን የሚያንጸባርቅ ነው፡፡ ይህ አቅጣጫ የሚያያዘው በጊዜው ከነበረው የባህታዊ አኗኗር ዘዬ ጋር ነው፡፡ በበረሃ ይኖሩ ከነበሩት መኖክሴዎች ውስጥ አንዱ ቅዱ ኤለሰባን ነው፡፡ የበረሃ ላይ የብቸኝነት ህይወት በጣም ውብ፣ በመለኮት የተጥለቀለቀ፣ በብርሀን የተሞላ እና በጥልቀት የሚመረመርበት ነው፡፡ በብቸኝነት ክብር የተከለለ እና በሚሰጥር የምስራቅ ህዝብን የሚከብ ነው፡፡

A ceremonial fan showing saints of Ethiopia 

ልክ ጸጋ የስፔይን ነፍስ ስትነካ በህይወት ሲፈነዳ ያለው ውበት፣ ጸጋ በፈረንሳይ ስዎች ላይ ሲወርድ ግርማን እንደሚያላብሰው ልክ እንደዛው ጸጋ የምስራቅ ሰዎችን አስተሳሰብ ቅርጽ እንደሚያሲዘው በቅዱስ ኢለባን ህይወትም ላይ ማየት ይቻላል፡፡ ግን የጥንቷን ኢትዮጵያ ከቸሁኗ ጋር ስናወዳድረው ሀዘንን ይፈጥራል፡፡
የዛኔዋ አትዮጵያ ትመራ የነበረው በታላቅ ኦርቶዶክስ ንጉስ ትመራ ነበር፡፡ ለሀገሩ ህይወት አስፈላጊ ነበር፣ ፍትሃዊ መሪ፣ታላቅ ተዋጊ፣ ይሱ ተኪ እንዲሆን ልጁን ያስተማረ ብልህ አባት ነበር፡፡ ንግስናውን ከተወ በኋላ ወደ በረሃ ሄደ፡፡
ታላቁ ንጉስ የመስቀል ተዋጊም ነበር፡፡ አረቢያ ውስጥ የጀመረው የሃይማኖት ግድያ በአይሁድ ሀይማኖት ወገን የተነሳሳ ሲሆን የሚያስተላልፈውም ግድፈትንና በደቡብ አረቢያ የኡሁኗ የመን፣ የሚገኘውን የኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ማውደም ነበር፡፡ በምስራቅ የሮማን ንጉስ ይነበረው ሱዜሬን የኢትዮጵያውን ንጉስ ኤለሰባንን ይህን እልቂት እንዲያቆመው አዘዘው፡፡
በምዕራብ ቀይ ባህር ዳርቻ አካባቢ የክርስትና ቅስቀሳ ተቋቁሞ ነበር፡፡ ቅዱስ ኤለስባንም እንደኮከብ ያበራ ነበር፡፡ በምስራቅ ዳርቻ ደግሞ ያረቢያ የጥፋት ቡድን ነበረ፡፡ የዛ ዘመን አረብያ ብዙ ታማኝ ቅዱሳን የነበሯት ሲሆን ስነስም ተገድለዋል፣ ከስልጣናቸው ወርደዋል ወይም ተሰውተዋል፡፡
ከዛም እውነተኛ የመስቀል ተዋጊ መጣና ያለአግባብ ነጠቂዎቹን አሸነፈ፣ ግድፈቱን ደመሰሰ፣ ጳጳሱን ወደ ደብራቸው መለሰ እናም ስርአትን እንደገና መሰረተ፡፡ እንደቅዱስ ኤለሰባን አይነት ታላቅ ንጉስ ለኢትዮጵያ ክብር ነው፡፡
      
Medieval depictions of ethiopian warriors 

ይህ የተፈጠረው በ 6ኛው ክፍለዘመን ነበር፡፡ ክ 2 ክፍለዘመናት በፊት ቅዱስ ፍሩመንቲየስ ኢትዮጵያንን ወደ ኦርቶዶክስ ሀይማኖት ለውጦ ነበር፡፡ የብዙ ቅዱሳንም መድመቂያ ነበር፡፡ አንዱም ቅዱስ ኤለስባን ነው፡፡ በ7ኛው እና 8ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ጥሩው ክፍል በሙስሊም የበላይነት ስር ትወድቅ ነበር፡፡ ለብዙም ክፍለ ዘመናት የሃይማኖቱ ጉዳይ አደናጋሪ ነበር፡፡
ተጠራጣሪዎቹ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ባህሪይ እንዳለው ካዱ - ሰውና አምላክ፤ ሁለት ሳይሆን አንድ ባህርይ ነው ያለው አሉ፡፡
በመጀመሪያ እኛ የምእራብ ያለነው ስዎች በምስራቅ ያሉ ስዎች የኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን አባላት አድርገን አናያቸውም፡፡ ቤተ ክርስቲያንን የላቲን አድርገን ዕናያለን፡፡ ይህ ስህተት ነው፡፡ ለቤተ-ክርስቲያክ ታማኝ ለመሆን 1 ሁኔታ ብቻ ነው የሚፈለገው፣ ለመለኮታዊ ጸጋ ራስን ማስገዛት፡፡ ማንም ሰው በኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ማደግና ጫፍ መድረስ ይችላል፡፡
  ሁለተኛ በቅዱስ ኤለስባን ማንም ሰው የብቸኝነትን ትልቅነት ማይት ይችላል፡፡ ግዛቱን የለቀቀው ከነክብሩ ነው፡፡
 
 A ruined monastery set in a desert cliff


ሶስተኛ፣ የሱ ህይወት የጥቁር ዘር ትልቅ ሚና፣ የጥቁር ስነ ልቦና ያሳያል፡፡ ይህን ለመረዳት እንደችግር መታየት  ያለበት እንደ አሜሪካውያን አጉል ዘመናዊ ለመሆን መተግበር የለብንም፡፡ እንዲያውም ማየት ያለብን ጥቁሩ ማጊ ኪንግ  ባልታዛር ክዋክብትን ከምስራቅ ወደ መለኮታዊው ህጻን ተከትሎ እንደሄደው ነው፡፡